Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 6:46

[1] ከዚህም በኋላ አጵሎስ በቆሮንቶስ ሳለ፥ ጳውሎስ ላይ ላዩን ሄዶ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ በዚያም ጥቂት ደቀ መዛሙርትን አገኘ።

[2] “ካመናችሁ ጀምሮ በውኑ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋልን?” አላቸው፤ እነርሱም ፥ “አልተቀበልንም መንፈስ ቅዱስ እንዳለ ስንኳ አልሰማንም ” አሉት።

[3] እርሱም ፥ “እንኪያ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው፤ እነርሱም ፥ “በዮሐንስ ጥምቀት ” አሉት።

[4] ጳውሎስም ፥ “ዮሐንስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ እየሰበከ የንስሓ ጥምቀትን አጠመቀ ” አላቸው።

[5] እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ።

[6] ጳውሎስም እጁን በጫነባቸው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ፤ ያንጊዜም በሀገሩ ሁሉ ቌንቌ ተናገሩ፤ ትንቢትም ተናገሩ።

[7] ሰዎቹም ሁሉ ዐሥራ ሁለት ያህሉ ነበር።

[8] ጳውሎስም ወደ ምኵuራብ ገብቶ በግልጥ አስተማረ፤ ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት እያስተማራቸውና እያሳመናቸው ሦስት ወር ቈየ።

[9] በተሰበሰበውም ሕዝብ ፊት አንዳንዶች በእግዚአብሔር ትምህርት ላይ ክፉ እየተናገሩ ባላመኑ ጊዜ፥ ጳውሎስ ከእነርሱ ተለየ፤ ደቀ መዛሙርቱንም ይዞ ጢራኖስ በሚባል መምህር ቤት ሁልጊዜ ያስተምራቸው ነበር።

[10] በእስያም ያሉ አይሁድና አረማውያን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል እስኪሰሙ ድረስ እንደዚሁ ሁለት ዓመት ኖረ።

[11] እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ ታላላቅ ሥራን ይሠራ ነበር።

[12] ከልብሱ ዘርፍና ከመጠምጠሚያዉ ጫፍ ቈርጠው እየወሰዱ በድውያኑ ላይ ያኖሩት ነበር፤ እነርሱም ይፈወሱ ነበር፤ ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።

[13] ከአይሁድም አስማት እያደረጉ የሚዞሩ ሰዎች ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ “ጳውሎስ በሚያስተምርበት በኢየሱስ ስም እናምላችኋለን ” እያሉ የጌታችን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ነበር።

[14] እኒህ እንዲህ ያደርጉ የነበሩትም የካህናቱ አለቃ የአይሁዳዊው የአስቂዋ ልጆች ናቸው፤ እነርሱም ሰባት ነበሩ።

[15] ያም ክፉ መንፈስ ፥ “በኢየሱስ አምናለሁ፥ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እንግዲህ እናንተ እነማን ናችሁ?” ብሎ መለሰላቸው።

[16] ያም ክፉ መንፈስ የያዘው ሰው ተነሣባቸው፤ አየለባቸውም፤ አሸነፋቸውም፤ አቐስሎም ከዚያ ቤት አስወጥቶ አባረራቸው።

[17] ይህም ነገር በኤፌሶን በሚኖሩ በአይሁድና በአረማውያን ሁሉ ዘንድ ተሰማ፤ ሁሉም ፈሩ፤ የጌታችን የኢየሱስንም ስም ከፍ ከፍ አደረጉ።

[18] ያመኑትም ሁሉ እየመጡ ስለ ሠሩት ንስሓ ይገቡ ነበር።

[19] ብዙዎች አስማተኟችም መጽሐፎቻቸውን እየሰበሰቡ እያመጡ በሕዝቡ ሁሉ ፊት በእሳት ያቃጥሉ ነበር፤ ያቃጠሏቸው የመጽሐፎች ዋጋም አምሳ ሺህ ብር ነበር።

[20] እንዲህም እያለ የእግዚአብሔር ቃል በኀይል ያድግና ይበረታ ነበር።

[21] ይህም ከተፈጸመ በኋላ ጳውሎስ በመቄዶንያና በአካይያ በኩል አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም ሊሄድ በልቡ ዐሰበ ፥ “እዚያም ከደረስሁ በኋላ ሮሜን ላያት ይገባኛል ” አለ።

[22] ከሚያገለግሉትም ሁለቱን ጢሞቴዎስንና አርስጦስን ወደ መቄዶንያ ላከ፤ እርሱ ራሱ ጳውሎስ ግን ብዙ ቀን በእስያ ተቀመጠ።

[23] በዚያም ወራት ስለዚህ ትምህርት ብዙ ሁከት ሆነ።

[24] በዚያም ብር ሠሪ የሆነ ድሜጥሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ ለአርጤምስም ከብር የቤተ መቅደስ ምስል ይሠራ ነበር፤ አንጥረኟችንም እያሠራ ብዙ ገንዘብ ይሰጣቸው ነበር።

[25] አንጥረኟችንና ይህን የመሰለውን ሥራ የሚሠሩትንም ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው ፥ “እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ጥቅም የምናገኘው በዚህ ሥራችን እንደ ሆነ እናንተ ታውቃላችሁ።

[26] አሁን ግን እንደምታዩትና እንደምትሰሙት ይህ ጳውሎስ ኤፌሶንን ብቻ ሳይሆን መላውን እስያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝብንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚሠሩትንም ሁሉ አማልክት አይደሉም አላቸው።

[27] አሁን የምንቸገር በዚህ ነገር ብቻ አይደለም፤ እስያና መላው ዓለም የሚያመልካት የታላቌ የአርጤምስም መቅደስ ክብር ይቀራል፤ ገናናነቷም ይሻራል።”

[28] ይህንም በሰሙ ጊዜ ተቈጡና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ፥ “የኤፌሶን አርጤምስ ክብርዋ ታላቅ ነው ” አሉ።

[29] ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ የመቄዶንያን ሰዎች የጳውሎስን ወዳጆች ጋይዮስንና አርስጥሮኮስንም ከእነርሱ ጋር እየጐተቱ በአንድነት ወደ ጨዋታው ቦታ ሮጡ።

[30] ጳውሎስም ወደ አሕዛብ መካከል ሊገባ ወድዶ ነበር፤ ነገር ግን ደቀ መዛሙርት ከለከሉት።

[31] ከእስያም የሆኑ ታላላቆች ወዳጆቹ ወደ ጨዋታው ቦታ እንዳይገባ ልከው ማለዱት።

[32] በዚያም በጨዋታው ቦታ የነበሩ ሰዎች እየጮኹ ቈዩ፤ በሌላም ቌንቌ የሚጮሁ ነበሩ፤ በጉባኤው ታላቅ ድብልቅልቅ ሆኖ ነበርና፤ ከእነርሱ የሚበዙት ግን በምን ምክንያት እንደ ተሰበሰቡ አያውቁም ነበር።

[33] በዚያ የነበሩ አይሁድም እስክንድሮስ የሚባል አይሁዳዊ ሰውን ከመካከላቸው አስነሡ፤ እርሱም ተነሥቶ በእጁ ምልክት ሰጠና ለሕዝቡ ሊከራከርላቸው ወደደ።

[34] አይሁዳዊ እንደሆነም ባወቁ ጊዜ “የኤፌሶን አርጤምስ ክብርዋ ታላቅ ነው ” እያሉ ሁለት ሰዓት ያህል ሁሉም በአንድ ድምፅ ጮሁ።

[35] ከዚህም በኋላ የከተማው ጸሓፊ ተነሥቶ ሕዝቡን ጸጥ አሰኝቶ እንዲህ አላቸው ፥ “እናንተ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፥ ስሙ፤ የኤፌሶን ከተማ ታላቂቱን አርጤምስንና ከሰማይ የወረደውን ጣዖትWaን እንደምትጠብቅ የማያውቅ ማነው?

[36] ስለዚህም እርስዋን መቃወም የሚቻለው ያለ አይመስለኝም፤ አሁንም ይህን በጠብና በክርክር ሳይሆን በቀስታ ልናደርገው ይገባናል።

[37] የአማልክትን ቤት ያልዘረፉትንና በአማልክቶቻችን ላይ ክፉ ቃልን ያልተናገሩትን እነዚህን ሰዎች እነሆ ወደ እዚህ አምጥታችኋቸዋል።

[38] ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉ አንጥረኟች ግን በማንም ላይ ጠብ እንዳላቸው እርስ በርሳቸው ይከራከሩ፤ እነሆም በከተማው ውስጥ ፍርድ ቤት አለ፤ ዳኟችም አሉ።

[39] ነገር ግን ይህ የምትከራከሩበት ነገር ሌላ ከሆነ በሕግ ሸንጎ ይፈታል።

[40] ዛሬም በደል ሳይኖር በአመጣችሁብን ክርክር እኛ እንቸገራለንና ስለዚህ ክርክር የምንወቃቀሰው ነገር የለም፥” ይህንም ብሎ ሸንጎውን ፈታ።

የሐዋርያት ሥራ። — Chapters