Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 3:34

[1] በጉም ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱ እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ ፥ “መጥተህ እይ ” ሲል ሰማሁ።

[2] እነሆ፥ አምባላይ ፈረስ ሲወጣ አየሁ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ይዞአል፤ አክሊልም ተሰጠው፥ ድል ሊነሣም ወጣ፥ ድልም ነሣ።

[3] ሁለተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ከእንስሳቱ መካከል ሁለተኛው እንስሳ ፥ “መጥተህ እይ ” ሲል ሰማሁ።

[4] ሌላም ዳማ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ ለተቀመጠው ሰላምን ከምድር ይወስድ ዘንድ፥ ሰዎችም እርስ በርሳቸው እንዲተራረዱ ሥልጣን ተሰጠው፤ ታላቅ ሰይፍም ሰጡት።

[5] ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ከእንስሳቱ ሦስተኛው እንስሳ ፥ “መጥተህ እይ ” ሲል ሰማሁ፥ አየሁም ፥ እነሆ ዱሪ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞአል።

[6] በአራቱ እንስሶችም መካከል እንደ ንስር ድምፅ ፥ አንድ ርቦ ስንዴ በዲናር፥ ሦስት ርቦ ገብስም በዲናር፥ ዘይትንና ወይንንም አታጥፋ ሲል ሰማሁ።

[7] አራተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ የአራተኛው እንስሳ ድምፅ ፥ “መጥተህ እይ ” ሲል ሰማሁ።

[8] አየሁም ፥ እነሆም፥ ሐመር ፈረስ ወጣ፤ በላዩ የተቀመጠውም ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ትከተለዋለች በጦርና በረኀብ፥ በሞትም፥ በምድር አራዊትም ይገድሏቸው ዘንድ በምድር አራተኛ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።

[9] አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የተገደሉትን ሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያዉ በታች አየሁ።

[10] በታላቅ ድምፅም እየጮሁ ፥ “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ስለ ደማችንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” አሉ።

[11] ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀሮቻቸውና የወንድሞቻቸው ቐጥር እስኪፈጸም ድረስ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተነገረላቸው።

[12] ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ዳግመኛ ታላቅ መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ማቅ ጥቁር ሆነ፤ ጨረቃም ሁለንተናው እንደ ደም ሆነ። ማቴ.

[13] ከዋክብትም ጽኑ ነፋስ በመታው ጊዜ ያልደረሰ ፍሬውን እንደሚያረግፍ በለስ ከሰማይ ረገፉ።

[14] ሰማይም እንደሚጠቀለል ብራና ተጠቀለለች፤ ተራሮችና ደሴቶችም ሁሉ ከስፍራቸው ተወገዱ።

[15] የምድር ነገሥታትና መሳፍንት፥ አለቆችና ባለጠጎችም፥ ታላላቆችም፥ ባሪያዎችና ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለቶች ሥር ተደበቁ።

[16] ተራሮችንና ዐለቶችን፥ ዋሻዎችንም ፥ “በእኛ ላይ ውደቁ፥ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት፥ ከበጉም ቅWጣ ሰውሩን፤

[17] ታላቂቱ የፍርድ ቀን ደርሳለችና፥ ማን ሊቃወማት ይችላል?” አሉአቸው።

የዮሐንስ ራእይ። የዮሐንስ ራእይ — Chapters