Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 5:09

[1] ከዚህም በኋላ አዲስ ሰማይንና አዲስ ምድርን አየሁ፤ የፊተኛው ሰማይና የፊተኛዪቱ ምድር አልፈዋልና፤ ባሕርም ወደፊት የለችም።

[2] ቅድስቲቱም ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ፤ ለባልዋ እንደ አጌጠች ሙሽራም ተዘጋጅታ ነበር።

[3] ከሰማይም እንዲህ የሚል ታላቅ ድምፅን ሰማሁ፤ “እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ። እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል።

[4] ከዐይኖቻቸውም እንባን ሁሉ ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህም ሞት የለም፤ ኀዘንም ቢሆን፥ ጩኸትም ቢሆን፥ ሕማምም ቢሆን ከእንግዲህ ወዲህ የለም፤ የቀድሞው ሥርዐት አልፎአልና፤ እነሆም ሁሉ ታደሰ።”

[5] በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው እንዲህ አለ ፥ “እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ፤” ለእኔም እንዲህ አለኝ ፥ “ይህ ቃል የታመነና እውነተኛ ነውና ጻፍ።”

[6] እንዲህም አለኝ ፥ “ተፈጽሞአል፤ አልፋና ዖሜጋ፥ ቀዳማዊና ደኃራዊ እኔ ነኝ፤ እኔም ለተጠማው ይጠጣ ዘንድ ከሕይወት ውኃ ምንጭ ያለዋጋ እሰጠዋለሁ።

[7] ድል የሚነሣም ይህን ይወርሳል፤ ለእርሱም አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።

[8] ነገር ግን የሚፈሩና የማያምኑ፥ የርኩሳንም፥ የነፍሰ ገዳዮችም፥ የሴሰኟችም፥ የአስማተኟችም፥ ጣዖትንም የሚያመልኩ፥ የሐሰተኟችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ውስጥ ነው፤ ይኸውም ሁለተኛ ሞት ነው።”

[9] የኋለኟቹን ሰባት መቅሠፍታት የተሞሉ ሰባት ጿዎችን ከያዙ ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጣ፤ እንዲህም ተናገረኝ ፥ “በጉ የተሠዋላትን ሙሽራ ሴት አሳይህ ዘንድ ወደዚህ ና።”

[10] በመንፈስም ወደ ረዥምና ወደ ታላቅ ተራራ ወሰደኝ፤ ቅድስቲቱንም ከተማ ኢየሩሳሌምን ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ ስትወርድ አሳየኝ፤

[11] የእግዚአብሔርም ክብር በእርስዋ ላይ አለ፥ ብርሃንዋም እጅግ እንደ ከበረ ዕንቐ እንደ ኢያሰጲድ ዕንቐ ሆኖ እንደ ብርሌ የጠራ ነው።

[12] ታላቅና ረዥም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለት በሮችም ነበሯት፤ በየበሮችም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆመዋል፤ የዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞችም ተጽፈውባቸው ነበር።

[13] በምሥራቅም ሦስት በሮች፥ በምዕራብም ሦስት በሮች፥ በሰሜንም ሦስት በሮች፥ በደቡብም ሦስት በሮች ነበሩ።

[14] የከተማይቱ ቅጽር መሠረቶችም ዐሥራ ሁለት ነበሩ፤ የዐሥራ ሁለቱም የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈውባቸዋል።

[15] ከእኔም ጋር የሚነጋገረው ከተማይቱንና በሮችዋን፥ ቅጽሮችዋንም የሚለካበትን የወርቅ ዘንግ ይዞአል።

[16] ከተማይቱም አራት መዓዝን ነበረች፤ ርዝመቷም እንደ ስፋቷ ልክ ነበረ፤ ከተማይቱንም በዘንግ ለካት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ምዕራፍ ሆነች፤ ርዝመቷና ስፋቷ ከፍታዋም ትክክል ነው።

[17] ከዚህም በኋላ ቅጽርዋን ለካ፤ በሰው ክንድ መቶ አርባ አራት ነው፤ ይኸውም በመልአኩ ክንድ አንድ ክንድ ነው።

[18] የከተማዋ ቅጽር ክባስም በኢያሰጲድና በያክንት፥ በመረግድም የተሠራ ነበረ። ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች።

[19] የከተማይቱም ቅጽር መሠረት እንደ ብርሌ ነጭ ነበር፤ በከበረም ዕንቅW ሁሉ ያጌጠች ነበረች፤ የመጀመሪያዪቱ መሠረት በኢያሰጲድ፥ ሁለተኛዪቱም በሰንፔር፥ ሦስተኛዪቱም በኬልቄዶን፥ አራተኛዪቱም በመረግድ።

[20] አምስተኛዪቱ በሰርዶንክስ፥ ስድስተኛዪቱ በሰርድዮን፥ ሰባተኛዪቱም በክሪስቲሎቤ፥ ስምንተኛዪቱም በቢረሌ፥ ዘጠነኛዪቱም በወራውሬ፥ ዐሥረኛዪቱም በክርስጵራስስ፥ ዐሥራ አንደኛዪቱም በያክንት፥ ዐሥራ ሁለተኛዪቱም በአሜቴስጢኖስ የተሠራች ነበረች።

[21] ዐሥራ ሁለቱ ደጆችዋም በዐሥራ ሁለት ዕንቐዎች የተጌጡ ነበሩ፤ እያንዳንዱም ደጅ ከአንድ ዕንቅW የተሠራ ነበረ፥ የከተማይቱም ዐደባባይ ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበር።

[22] ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔርና በጉ መቅደስዋ ናቸውና በእርስዋ ዘንድ መቅደስ አላየሁም።

[23] ከተማይቱም ያበሩላት ዘንድ ፀሓይን፥ ወይም ጨረቃን አትሻም፤ የእግዚአብሔር ብርሃን ያበራላታልና፤ በጉም መብራቷ ነውና።

[24] አሕዛብም በብርሃንዋ ይመላለሳሉ፤ የምድር ነገሥታትም ክብራቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ።

[25] በዚያም ሌሊት ስለሌለ በሮችዋ በቀን አይዘጉም።

[26] አሕዛብም ክብራቸውንና ግርማቸውን ወደ እርስዋ ያመጣሉ።

[27] በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር ጸያፍ ነገር ሁሉ፥ ርኵuሰትና ውሸትም የሚያደርግ ወደ እርስዋ ከቶ አይገባም።

የዮሐንስ ራእይ። የዮሐንስ ራእይ — Chapters