Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 2:49

[1] ከዚህ በኋላም በሰማይ የተከፈተች በር አየሁ፤ እንደ መለከትም ድምፅ ያለውን ፊተኛውን ድምፅ ሰማሁ፤ ከእኔም ጋር ይነጋገር ነበር፤ እንዲህም አለኝ ፥ “ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን ያለውን እኔ አሳይሃለሁ።”

[2] ያንጊዜም በመንፈስ ነበርሁ፤ እነሆ፥ ዙፋን በሰማይ ተዘርግቶ ነበር፤ በላዩም ተቀማጭ ነበረ።

[3] ተቀምጦም የነበረው መልኩ የኢያሰጲድና የሰርዲኖን ዕንቅW ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ መልኩ መረግድን የመሰለ ቀስተ ደመና ነበረ።

[4] በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ወንበሮች ነበሩ፤ በእነዚያ ወንበሮች ላይም ሃያ አራት አለቆች ተቀምጠዋል፤ ነጭ ልብስም ለብሰዋል፤ በራሶቻቸውም ላይ የወርቅ አክሊሎች ደፍተው ነበር።

[5] ከዙፋኑም መብረቅና ብልጭልጭታ፥ ነጐድጓድም ይወጡ ነበር፤ በዙፋኑ ፊትም ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር፤ ይኸውም የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ነው።

[6] በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ፤ በዙፋኑም መካከል፥ በዙፋኑም ዙሪያ አራቱ እንስሶች አሉ፤ እነርሱም በፊትም፥ በኋላም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው።

[7] ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ ሰውን ይመሳል፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበር ንስርን ይመስላል።

[8] ለእነዚህም አራቱ እንስሶች ለእያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ በሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለው፥ የሚመጣውም፥ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ ” እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።

[9] እነዚህ እንስሶችም በዙፋን ላይ ለተቀመጠው፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሕይወት ለሚኖረው ለእርሱ ክብርና ውዳሴን ምስጋናንም ይሰጣሉ።

[10] እነዚያም ሃያ አራቱ አለቆች፥ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ወድቀው ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ለእርሱ አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት አውርደው ይሰግዳሉ።

[11] እንዲህም ይላሉ ፥ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ሆነዋልና፥ ተፈጥረውማልና ክብርና ውዳሴ ኀይልም ለአንተ ይገባል።”

የዮሐንስ ራእይ። የዮሐንስ ራእይ — Chapters