Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 3:52

[1] ለእነዚያም ለሰባቱ መላእክት ፥ “ሂዱ፥ የእግዚአብሔርን ቅWጣ ጿዎች በምድር ሁሉ አፍስሱ ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ከመቅደሱ ሰማሁ።

[2] ፊተኛውም መልአክ ሔዶ፥ ጿውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የዚያን አውሬ ምልክት በአጻፉ፥ ለምስሉም በሰገዱ በእነዚያ ሰዎች ላይ ክፉ ቐስል መጣባቸው።

[3] ሁለተኛውም መልአክ ጿዉን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ ባሕርም እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነች፤ በባሕር ውስጥ የሚኖረው ሕይወት ያለው ፍጥረትም ሁሉ ሞተ።

[4] ሦስተኛው መልአክም ጿውን በወንዞችና በምንጮች ላይ አፈሰሰ፤ ወንዞችና ምንጮችም ሁሉ ደም ሆኑ።

[5] የውኃዎች ምንጮች መልአክም ፥ “ያለህና የነበርህ አምላክ ሆይ፥ ቅዱስ ሆይ፥ እንዲህ ስለ ፈረድህ ጻድቅ ነህ።

[6] የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም አፍስሰዋልና ደምን አጠጣሃቸው፤ የሚገባቸው ነውና ” ብሎ ሲናገር ሰማሁ።

[7] በመሠዊያው ውስጥም እንዲህ የሚል ቃል ሰማሁ ፥ “አዎን፥ አቤቱ፥ ሁሉን የምትገዛ እግዚአብሔር ሆይ፥ ፍርድህ እውነትና ቅን ነው።”

[8] አራተኛው መልአክም ጿዉን በፀሓይ ላይ አፈሰሰ፤ ሰውንም በእሳት ያቃጥለው ዘንድ ግለት ተሰጠው።

[9] ሰዎችም በታላቅ ትኵuሳት ተቃጠሉ፤ በእነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም ይሰጡት ዘንድ ንስሓ አልገቡም።

[10] አምስተኛው መልአክም ጿዉን በዚያ አውሬ ዙፋን ላይ አፈሰሰው፤ ሰዎችም በሕማም መላሳቸውን እስኪአላምጡ ድረስ መንግሥቱ ጨለማ ሆነች።

[11] ከሥቃያቸውና ከቐስላቸውም የተነሣ፥ የሰማይ ጌታን እስኪነቅፉ ድረስ፥ ከሥራቸው አልተመለሱም።

[12] ስድስተኛው መልአክም በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ ጿዉን አፈሰሰ፤ ከፀሓይ መውጫ ለሚመጡ ነገሥታትም መንገድ ያዘጋጅላቸው ዘንድ ውኃው ደረቀ።

[13] ከዚህም በኋላ ከዚያ ከፊተኛው አውሬ አፍ፥ ከአንበሳውም አፍ፥ ከሐሰተኛው ነቢይም አፍ ጓጉንቸር የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን አጋንንት ሲወጡ አየሁ፤

[14] ምልክትም እያደረጉ፥ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።

[15] “እነሆ፥ እንደ ሌባ ድንገት እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሔድ፥ ኀፍረቱንም እንዳይገልጥ፥ ተግቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”

[16] በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ቦታ እሰበስባቸዋለሁ።

[17] ሰባተኛው መልአክም ጿዉን በአየር ላይ አፈሰሰ፤ ከመቅደሱም ውስጥ ፥ “ተፈጸመ ” የሚል ታላቅ ድምጽ ከዙፋኑ ወጣ።

[18] ከዚህም በኋላ መብረቅ፥ የነጐድጓድም ድምፅ ሆነ፤ ታላቅ የምድር መናወጥም ሆነ፤ የሰውም ልጅ በምድር ላይ ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ያለ ታላቅ መናወጥ አልሆነም፤ ከእንግዲህም ወዲህ እንደዚያ ያለ ታላቅ መናወጥ አይሆንም።

[19] ታላቂቱም ከተማ ከሦስት ተከፋፈለች፤ የአሕዛብ ከተሞችም ወደቁ፤ የእግዚአብሔርም የቅWጣው ወይን መርዝ የተሞላበትን ጿ ትቀበል ዘንድ ታላቂቱን ባቢሎንን በእግዚአብሔር ፊት አሰቡአት፤

[20] ደሴቶችም ሁሉ ጠፉ፤ ተራሮችም አልተገኙም።

[21] በሚዛንም አንድ ታላንት የሚያህል ታላቅ በረዶ በሰዎች ላይ ከሰማይ ወረደባቸው፤ ሰዎቹም ከበረዶው መቅሠፍት የተነሣ እግዚአብሔርን ተሳደቡ፤ መቅሠፍቱ እጅግ ታላቅ ነበርና።

የዮሐንስ ራእይ። የዮሐንስ ራእይ — Chapters