[1] እነሆ፥ በጉ በጽዮን ተራራ ላይ ቆሞ አየሁ፤ ከእርሱም ጋር ስሙና የአባቱ ስም የመንፈስ ቅዱስም ስም በግንባራቸው የተጻፈባቸው መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
[2] እንደ ብዙ ውኃም ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ ያለ ከሰማይ ድምፅን ሰማሁ ደርዳሪዎችም እንደሚደረድሩት በገና ድምፅ ያለ ሰማሁ።
[3] በዙፋኑም ፊት በአራቱ እንስሶችና በአለቆቹ ፊት አዲስ ምስጋናን አመሰገኑ። ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራቱ ሺህ በቀር ያን ምስጋና ሊያውቅ ለማንም አልተቻለውም።
[4] ከሴቶችም ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ደናግል ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው፤ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵuራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።
[5] በአንደበታቸውም ሐሰት አልተገኘም፤ ነውር የለባቸውምና።
[6] ከዚህም በኋላ ሌላ መልአክ በሰማይና በምድር መካከል እየበረረ መጣ፤ በምድር ለሚኖሩ አሕዛብና ሕዝብ፥ በየሀገሩም ለሚኖሩ ወገን ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘለዓለምን ወንጌል ይዞአል።
[7] እንዲህ እያለም በታላቅ ድምፅ ጮኸ ፥ “እግዚአብሔርን ፍሩት፤ አመስግኑትም፤ የጽኑ ፍርድ ሰዓት ደርሳለችና፤ ሰማዩንና ምድሩን፥ ባሕሩንና ወንዞችን፥ የውኃ ምንጮችንም ለፈጠረ ለእርሱ ስገዱለት።
[8] ሌላም ሁለተኛ መልአክ ፥ “ከጥፋቷና ከዝሙቷ ወይን ለአሕዛብ ሁሉ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች ” እያለ ተከተለው።
[9] ሦስተኛው መልአክም በታላቅ ቃል እንዲህ እያለ ተከተላቸው ፥ “ለዚያ አውሬና ለምስሉ የሚሰግድ፥ በግንባሩ ወይም በእጁ የስሙ ምልክት የተጻፈበት፥
[10] እርሱ ያልተበረዘውንና በቅWጣው ጿ የተቀዳውን የእግዚአብሔርን የቅWጣውን ወይን ይጠጣል፤ በቅዱሳን መላእክቱና በበጉም ፊት በእሳትና በዲን ይሠቃያል።
[11] የሥቃያቸው ጢስም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ይወጣል፤ ለዚያ አውሬና ለምስሉ የሚሰግዱ፥ የስሙንም ምልክት የሚጽፉ በመዓልትም በሌሊትም ዕረፍት የላቸውም፤ ይህንም ፍርድ ይቀበላሉ።”
[12] የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁ፥ ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው ይህ ነው።
[13] ከሰማይም ቃል መጣ፥ እንዲህ የሚል ፥ “አሁን ጻፍ፤ ስለ እግዚአብሔር የሚሞቱ ብፁዓን ናቸው፤ አዎን መንፈስ ቅዱስ እንዲሁ ብሎአል፥ ከድካማቸው እንዲያርፉ ሥራቸው ይከተላቸዋል፤ ወደ ሕይወት ምንጭም ይወስዳቸዋል።”
[14] ብርህት ደመናም መጣች፤ በዚያች ደመና ላይም የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦ ነበር፤ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል አለ፥ በእጁም የተሣለ ማጭድ ይዞአል።
[15] ከእግዚአብሔርም መቅደስ ሌላ መልአክ ወጣ፤ በደመና ላይ ለተቀመጠውም ፥ “የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ላክና እጨድ፤ የምድሪቱ መከር ደርሶአልና ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
[16] ከዚህም በኋላ ያ በደመና ላይ የተቀመጠው ማጭዱን በምድር ላይ አነሣ፤ ምድርም ታጨደች።
[17] ሌላ መልአክም በሰማይ ካለው መቅደሱ ወጣ፤ እርሱም ደግሞ የተሳለ ማጭድ ይዞአል።
[18] ሌላ መልአክም ከመሠዊያው ተከተለው፤ ይኸውም በእሳት ላይ ሥልጣን ያለው ነው፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፥ ያን የተሳለ ማጭድ የያዘውን በታላቅ ድምፅ ጠርቶ ፥ “ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና የተሳለ ማጭድህን ላክ፤ በምድር ያለውንም የወይን ዛፍ ዘለላዎችን ቐረጥ ” አለው፤
[19] ያም መልአክ ማጭዱን አነሣ፤ ወደ መሬትም አወረደው፤ በእርሱም የምድርን ወይን ፍሬ ቈረጠበት፤ በገናናው በእግዚአብሔር የቅWጣ መጭመቂያም ጨመረው።
[20] የወይኑም መጭመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፤ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሁኖ ከመጭመቂያው ወጣ።