Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 3:17

[1] ሌላ አውሬም ከባሕር ሲወጣ አየሁ፤ ዐሥር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት፤ በቀንዶቹም ላይ ዐሥር ዘውዶች ነበሩት፤ በራሶቹም ላይ የስድብ ስም ተጽፎበታል።

[2] ያየሁት አውሬም ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹም እንደ ድብ፥ አፉም እንደ አንበሳ ነበር፤ ፊተኛው ዘንዶም ኀይሉንና ዙፋኑን፥ ታላቅ ሥልጣንም ሰጠው።

[3] ከራሶቹም አንዱን ለሞት እንደ ታረደ ሆኖ አየሁ፥ ለሞቱ የሚያደርሰውም ቅWስል ተፈወሰ። ምድርም ሁሉ አውሬውን እየተከተለች አደነቀች።

[4] ለቀደመው ዘንዶም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣኑን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም ፥ “ይህን አውሬ ማን ይመስለዋል? ማንስ ሊዋጋው ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።

[5] ታላቅ ነገርንና ስድብን ይናገር ዘንድ አፍ ተሰጠው፤ የወደደውንም ተአምር ያደርግ ዘንድ ለአርባ ሁለት ወር ሥልጣን ተሰጠው።

[6] ከዚህም በኋላ በእግዚአብሔርና በስሙ ላይ፥ በማደሪያውም ላይ፥ በሰማይም በሚኖሩት ላይ የስድብን ቃል ይናገር ዘንድ አፉን ከፈተ።

[7] ከቅዱሳንም ጋር ይዋጋ ዘንድ፥ ድልም ያደርጋቸው ዘንድ ተሰጠው፤ በአሕዛብና በሕዝብ፥ በሀገሮችና በነገድ ሁሉ ላይም ሥልጣን ተሰጠው።

[8] ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በታረደው በግ የሕይወት መጽሐፍ ስሞቻቸው ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ ሁሉ ሰገዱለት።

[9] ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ።

[10] ይማርክ ዘንድ ያለው ማንም ቢኖር ይማረካል፤ በሰይፍ የሚገድል ማንም ቢኖር ይገደላል፤ የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት በዚህ ነው።

[11] ከዚህ በኋላ ሌላ አውሬ ከምድር ሲወጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶችን የሚመስሉ ሁለት ቀንዶችም ነበሩት፤ እንደ ዘንዶውም ይናገር ነበር።

[12] በቀደመው አውሬ ሥልጣንም በፊቱ ሁሉን ያደርጋል፤ ለሞት የሚያደርሰውም ቐስል ተፈወሰለት፤ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትንም ለቀደመው አውሬ እንዲሰግዱ ያደርጋል።

[13] እሳትን እንኳ ከሰማይ ወደ ምድር እስኪያወርድ ታላላቅ ተአምራትን ያደርጋል።

[14] በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ተአምራት የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታቸዋል፤ በሰይፍ ቈስሎ ለነበረውና ለዳነው ለአውሬውም ምስልን ይሠሩ ዘንድ በምድር የሚኖሩትን ያዝዛቸዋል።

[15] የአውሬውም ምስል ይናገር ዘንድ በአውሬው ምስል ውስጥ መንፈስን ያሳድርበት ዘንድ ተሰጠው፤ ለአውሬውም ምስል ያልሰገደውን ሁሉ እንዲገደሉ ያደርጋቸዋል።

[16] ታናናሾችና ታላላቆች፥ ባለጠጎችና ድሆችም፥ ጌቶችና ባሮችም ሁሉ በቀኝ እጆቻቸው፥ ወይም በግንባሮቻቸው ምልክት እንዲጽፉ ያደርጋል።

[17] የአውሬውም የስሙ ምልክት፥ ወይም የስሙ ቐጥር ከተጻፈባቸው በቀር መሸጥ፥ ወይም መግዛት የሚቻለው እንዳይኖር ያደርጋል።

[18] በዚህም ጥበብ አለ፤ አእምሮ ያለው የአውሬውን ቅWጥር ያውቃል፤ ቅWጥሩ የሰው ቅWጥር ነውና። ቅWጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው።

የዮሐንስ ራእይ። የዮሐንስ ራእይ — Chapters