Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 1:55

[1] ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቅWጣ በእነርሱ ስለሚፈጸም ኋለኛዎቹን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት ታዩ።

[2] ከዚህም በኋላ ብርሌ የምትመስል ባሕርን አየሁ፤ ከእሳትም ጋር የተዋሐደች ናት፤ ያን አውሬና ምስሉን፥ የስሙንም ቅWጥር ድል የነሡ እነዚያ በዚያች ባሕር ላይ ቆመዋል፤ የእግዚአብሔርንም የምስጋናውን መሰንቆ ይዘዋል።

[3] የእግዚአብሔርንም ባሪያ የሙሴን ምስጋናና የበጉን ምስጋና እንዲህ እያሉ ያመሰግናሉ ፥ “ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው

[4] ጌታ ሆይ፥ አንተን የማይፈራና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና በአሕዛብ ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለህ አንተ ነህ፥ አቤቱ ፍጥረትህ ሁሉ በፊትህ ይሰግዳሉ፤ ፍርድህ ተገልጦአልና።”

[5] ከዚህም በኋላ አየሁ፤ የምስክርም ድንኳን መቅደስ በሰማይ ተከፈተ።

[6] እነዚያ ሰባት መቅሠፍት የያዙ ሰባት መላእክትም ከመቅደስ ወጡ፤ ብሩህና ነጭ የሐር ልብስም ለብሰዋል፤ በደረታቸው ላይም የወርቅ ዝናር ታጥቀዋል።

[7] ከእነዚያ ከአራቱ እንስሶችም አንዱ፥ ለእነዚያ ለሰባቱ መላእክት፥ ለዘለዓለም ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔር ቅWጣ የተመላባቸውን ሰባት የወርቅ ጿዎች ሰጣቸው።

[8] ከዚህም በኋላ፥ ከኀይሉና ከጌትነቱ የተነሣ፥ መቅደሱ የእግዚአብሔርን የቅWጣውን ጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላእክት የተቀበሉት ሰባት መቅሠፍትም እስኪፈጸም ድረስ ወደ መቅደሱ መግባት የሚችል የለም። 6፥4።

የዮሐንስ ራእይ። የዮሐንስ ራእይ — Chapters