[1] ጌታችን ኢየሱስም ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደዚያ ገባ።
[2] አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳም ያን ስፍራ ያውቀው ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ብዙ ጊዜ ይሄድ ነበርና።
[3] ይሁዳም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ወታደሮችን ተቀበለ፤ ሎሌዎቻቸውንም በረዳትነት ወሰደ፤ ፋኖስና የችቦ መብራት፥ የጦር መሣሪያም ይዞ ወደዚያ ሄደ።
[4] ጌታችን ኢየሱስም የሚደርስበትን ሁሉ ዐውቆ ወደ እነርሱ ወደ ውጭ ወጣና ፥ “ማንን ትሻላችሁ?” አላቸው።
[5] “የናዝሬቱን ኢየሱስን ” ብለው መለሱለት፤ ጌታችን ኢየሱስም ፥ “እኔ ነኝ ” አላቸው፤ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም በዚያው አብሮአቸው ቆሞ ነበር።
[6] ጌታችን ኢየሱስም ፥ “እኔ ነኝ ” ባላቸው ጊዜ፤ ወደ ኋላቸው ተመልሰው በምድር ላይ ወደቁ።
[7] ከዚህም በኋላ እንደገና ፥ “ማንን ትሻላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፤ እነርሱም ፥ “የናዝሬቱን ኢየሱስን ” አሉት።
[8] ጌታችን ኢየሱስም ፥ “እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ እኔን የምትሹ ከሆነ እነዚህን ተዉአቸው፤ ይሂዱ ” አላቸው።
[9] ይህም ፥ “ከእነዚህ ከሰጠኸኝ አንድ ስንኳ አልጠፋም ” ያለው ቃሉ ይፈጸም ዘንድ ነው።
[10] ስምዖን ጴጥሮስም ሾተል ነበረው፤ ሾተሉንም መዝዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ መትቶ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠው፤ የዚህም አገልጋይ ስም ማልኮስ ይባል ነበር።
[11] ጌታችን ኢየሱስም ጴጥሮስን ፥ “ሾተልህን ወደ አፎቷ መልስ፤ አብ የሰጠኝን ጿ ሳልጠጣ እተወዋለሁን?” አለው።
[12] ጭፍሮችና የሺ አለቃው፥ የአይሁድም ሎሌዎች ጌታችን ኢየሱስን ይዘው አሰሩት።
[13] አስቀድሞም ወደ ሐና ወሰዱት፤ በዚያች ዓመት የካህናት አለቃ ለነበረው ለቀያፋ አማቱ ነበርና።
[14] ቀያፋም “ስለ ሕዝቡ ሁሉ አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል ” ብሎ አይሁድን የመከራቸው ነበር።
[15] ስምዖን ጴጥሮስና ሌላው ደቀ መዝሙርም ጌታችን ኢየሱስን ከሩቅ ተከተሉት፤ ያ ደቀ መዝሙር ግን በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀ ነበር፤ ከጌታችን ኢየሱስ ጋርም ወደ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ገባ።
[16] ጴጥሮስ ግን በስተውጭ በበሩ ቆሞ ነበር፤ ያም በሊቀ ካህናቱ ዘንድ ይታወቅ የነበረው ሌላው ደቀ መዝሙር ወጣና ለበረኛዪቱ ነግሮ ጴጥሮስን አስገባው።
[17] በረኛዪቱ አገልጋይም ፥ “አንተም ከዚያ ሰው ደቀ መዛሙርት ወገን አይደለህምን?” አለችው፤ እርሱም ፥ “አይደለሁም ” አላት።
[18] አገልጋዮችና ሎሌዎችም በዚያ ቆመው እሳት አንድደው ይሞቁ ነበር፤ የዚያች ሌሊት ብርድ ጽኑ ነበርና፤ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበረ።
[19] ሊቀ ካህናቱም ጌታችን ኢየሱስን ፥ ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ ትምህርቱ ጠየቀው።
[20] ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው ፥ “እኔ ለዓለም በግልጥ ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵuራብም፥ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም የተናገርሁት አንዳች ነገር የለም።
[21] እንግዲህ እኔን ለምን ትጠይቀኛለህ? የተናገርሁትን የሰሙኝን ጠይቃቸው፤ እኔም የተናገርሁትን እነሆ፥ እነርሱ ያውቃሉ።”
[22] ይህንም ባለጊዜ ከቆሙት ሎሌዎች አንዱ ፥ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልስለታለህን?” ብሎ ጌታችን ኢየሱስን በጥፊ መታው።
[23] ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ፥ “ክፉ ተናግሬ እንደ ሆንሁ ስለ ክፉ መስክርብኝ፤ መልካም ተናግሬ እንደ ሆንሁ ግን ለምን ትመታኛለህ?” አለው።
[24] ሐናም ጌታችን ኢየሱስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው።
[25] ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ “አንተስ ከእርሱ ደቀ መዛሙርት ወገን አይደለህምን?” አሉት፤ እርሱም ፥ “አይደለሁም ” ብሎ ካደ።
[26] ጴጥሮስ ጆሮውን ከቈረጠው ሰው ዘመዶች ወገን የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮችም አንድ ሰው ፥ “እኔ በአትክልት ቦታ ውስጥ ከእርሱ ጋር አይቼህ አልነበረምን?” አለው።
[27] ጴጥሮስም ደግሞ ካደ፤ ያንጊዜም ዶሮ ጮኸ።
[28] ጌታችን ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ፍርድ አደባባይ ወሰዱት፤ አይሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋሲካውን በግ ሳይበሉ እንዳይረክሱ ወደ ፍርድ አደባባይ አልገቡም።
[29] ጲላጦስም ወደ እነርሱ ወደ ውጭ ወጥቶ ፥ “ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደሉ ምንድነው?” አላቸው።
[30] እነርሱም ፥ “ክፉ የሠራ ባይሆንስ ወደ አንተ አሳልፈን ባልሰጠነው ነበር ” ብለው መለሱለት።
[31] ጲላጦስም ፥ “እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት” አላቸው፤ አይሁድም ፥ “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም ” አሉት።
[32] ይህም በምን ዐይነት ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት የተናገረው የጌታችን የኢየሱስ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
[33] ጲላጦስም እንደገና ወደ ፍርድ አደባባይ ገብቶ ጌታችን ኢየሱስን ጠራና ፥ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው።
[34] ጌታችን ኢየሱስም ፥ “ይህን የምትናገር ከራስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነገረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለሰለት።
[35] ጲላጦስም መልሶ ፥ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና ሊቃነ ካህናት አይደሉምን? Aረ ምን አድርገሃል?” አለው።
[36] ጌታችን ኢየሱስም ፥ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ በዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ ለአይሁድ እንዳልሰጥ አሽከሮቼ በተዋጉልኝ ነበር፤ አሁንም መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም ” ብሎ መለሰለት።
[37] ጲላጦስም ፥ “እንግዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላለህ፤ እኔ ስለዚህ ተወለድሁ፤ ስለዚህም ለእውነት ልመሰክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማኛል ” አለው።
[38] ጲላጦስም ፥ “እውነት ምንድነው?” አለው፤ ይህንም ተናግሮ ዳግመኛ ወደ አይሁድ ወጣና እንዲህ አላቸው ፥ “እኔ አንዲት ስንኳን በደል አላገኘሁበትም።
[39] ነገር ግን በየዓመቱ በፋሲካ በዓል ከእስረኟች አንድ እንድፈታላችሁ ልማድ አላችሁ፤ እንግዲህ የአይሁድን ንጉሥ ልፈታላችሁ ትወዳላችሁን?” አላቸው።
[40] ዳግመኛም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ፥ “በርባንን እንጂ ይህን አይደለም፤” አሉ፤ በርባን ግን ወንበዴ ነበር።