Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 3:29

[1] “እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ።

[2] በምትፈርዱት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፥ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርባችኋልና።

[3] በወንድምህ ዐይን ያለውን ጕuድፍ ለምን ታያለህ? በአንተ ዐይን ያለውን ምሰሶ ግን ለምን አታስተውልም?

[4] ወንድምህን በዐይንህ ያለውን ጕuድፍ ላውጣልህ ተወኝ እንዴት ትለዋለህ? እነሆም፥ በአንተ ዐይን ምሰሶ አለ።

[5] አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ በአንተ ያለውን ምሰሶ አውጣ፤ ከዚህ በኋላ በወንድምህ ዐይን ያለውን ጕuድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ።

[6] “በእግራቸው እንዳይረግጡት፥ ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቐአችሁንም በዕሪያዎች ፊት አታኑሩ።

[7] ለምኑ፥ ይሰጣችኋልም፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁም፤ ደጅ ምቱ፥ ይከፈትላችኋልም።

[8] የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛልና፥ ደጅ ለሚመታም ይከፈትለታልና።

[9] ከእናንተ ልጁ ዳቦ ቢለምነው ድንጋይ የሚሰጠው ሰው ማነው?

[10] ወይስ ዓሣ ቢለምነው እባብ ይሰጠዋልን?

[11] እንግዲህ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን ካወቃችሁ፥ በሰማያት ያለው አባታችሁማ ለሚለምኑት መልካሙን ነገር እንዴት አብልጦ ይሰጣቸው ይሆን?

[12] ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትወዱትን ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፥ ነቢያትም የሚያዝዙት ይህ ነውና።

[13] “በጠባቢቱ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የምትወስድ ሰፊ በር፥ ሰፊ መንገድም አለችና፤ ወደ እርስዋም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው።

[14] ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ፥ መንገድዋም ቀጭን ናትና፤ የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው።

[15] “የበግ ለምድ ለብሰው ወደ እናንተ ከሚመጡ ከሐሰተኟች ነቢያት ተጠንቀቁ፤ በውስጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵuላዎች ናቸው።

[16] ከፍሬያቸው ታውቌቸዋላችሁ፤ ከእሾህ ወይን፥ ከአሜከላም በለስ ይለቀማልን?

[17] እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍሬን ያፈራል።

[18] መልካምም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት፥ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም።

[19] መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል።

[20] እንግዲህ ከፍሬያቸው ታውቌቸዋላችሁ።

[21] “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ ከሚያደርግ በቀር አቤቱ! አቤቱ! የሚለኝ ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።

[22] በዚያች ቀን ብዙዎች አቤቱ! አቤቱ! በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን? በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን? በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

[23] ያንጊዜ ከቶ አላውቃችሁም፤ ዐመፅን የምታደርጉ ሁላችሁ ከእኔ ራቁ እላቸዋለሁ።

[24] ይህን ቃሌን ሰምቶ የሚያደርገው ሁሉ ቤቱን በዐለት ላይ የሠራ ብልህ ሰውን ይመስላል።

[25] ዝናም ዘነመ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፉት፤ ነገር ግን አልወደቀም፤ በዐለት ላይ ተመሥርቶአልና።

[26] ይህንም ቃሌን ሰምቶ የማያደርገው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።

[27] ዝናም ዘነመ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያንም ቤት ገፉት፤ ወደቀም፤ አወዳደቁም ታላቅ ሆነ።”

[28] ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር በፈጸመ ጊዜ ሕዝቡ በትምህርቱ ተደነቁ።

[29] እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና።

የማቴዎስ ወንጌል። — Chapters