Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 5:09

[1] “መንግሥተ ሰማያት ለወይኑ ቦታ ሠራተኟችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤት ሰውን ትመስላለች።

[2] ከሠራተኟችም ጋር በቀን አንድ ድሪም ሊሰጣቸው ተስማምቶ፥ ወደ ወይኑ ቦታ ላካቸው።

[3] በሦስት ሰዓትም በወጣ ጊዜ ሌሎችን በአደባባይ ቆመው ሥራ ፈትተው አየ።

[4] እነዚያንም ፥ እናንተም ወደ ወይኔ ቦታ ሂዱና ሥሩ፤ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው፤ እነርሱም ሄዱ።

[5] ዳግመኛም በስድስትና በዘጠኝ ሰዓት ወጥቶ እንዲሁ አደረገ።

[6] በዐሥራ አንድ ሰዓትም ወጥቶ ሌሎችን ቆመው አገኘ፤ ቀኑን ሁሉ ሥራ ፈትታችሁ ለምን በዚህ ቆማችኋል? አላቸው።

[7] እነርሱም ፥ የሚቀጥረን ስለ አጣን ነው አሉት፤ እርሱም ፥ እናንተ ወደ ወይኔ ቦታ ሂዱ፤ የሚገባውንም እሰጣችኋለሁ አላቸው።

[8] በመሸም ጊዜ የወይኑ ቦታ ባለቤት ሹሙን እንዲህ አለው፤ ሠራተኟቹን ጠርተህ አስቀድመህ ከኋለኟች ጀምረህ እስከ ፊተኟች ድረስ ደመወዛቸውን ስጣቸው።

[9] በዐሥራ አንድኛው ሰዓት የተቀጠሩትም መጡና እያንዳንዳቸው አንድ ዲናር ተቀበሉ።

[10] የቀደሙትም መጥተው ከእነዚያ ይበልጥ የሚያገኙ መስሎአቸው ነበር፤ እነርሱም እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ዲናር ተቀበሉ።

[11] ተቀብለውም በባለቤቱ ላይ አንጐራጐሩ።

[12] እንዲህ እያሉ ፥ እነዚህ ኋለኟች አንዲት ሰዓት ብቻ ሠሩ፤ የቀኑን ድካምና ሐሩር ከተሸከምነው ከእኛም ጋር አስተካከልሃቸው።

[13] እርሱ ግን ከእነርሱ አንዱን እንዲህ አለው ፥ ወዳጄ ሆይ፥ አልበደልሁህም፤ በአንድ ዲናር ተስማምቼህ የለምን?

[14] የሚደርስህን ይዘህ ሂድ፤ እኔም ለዚህ ለኋለኛው እንዳንተ ልሰጠው እወዳለሁ።

[15] ወይስ በገንዘቤ የወደድሁትን ላደርግ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ ቸር ስለሆንሁ ዐይንህ ምቀኛ ናትን?

[16] እንዲሁም ኋለኟች ፊተኟች ይሆናሉ፤ ፊተኟችም ኋለኟች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡም ጥቂቶች ናቸውና።”

[17] ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ለብቻቸው ወሰዳቸው፤ በመንገድም እንዲህ አላቸው ፥

[18] “እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች ተላልፎ ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል።

[19] ለሕዝቡም አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ይዘብቱበታል፤ ይገርፉታል፤ ይሰቅሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።”

[20] ከዚህም በኋላ፥ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆችዋ ጋር መጣች፤ ከእርሱም አንዳች ነገር እየለመነች ሰገደችለት።

[21] እርሱም ፥ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት፤ እርስዋም ፥ “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ በመንግሥትህ አንዱ በቀኝህ አንዱም በግራህ እንዲቀመጡ አድርግልኝ ” አለችው።

[22] ጌታችን ኢየሱስም መልሶ ፥ “የምትለምኑትን አታውቁም፤ እኔ የምጠጣውን ጿ መጠጣት ትችላላችሁን? እኔስ የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁን?” አላቸው። እነርሱም ፥ “አዎን፥ እንችላለን ” አሉት።

[23] እርሱም ፥ “ጿዬንስ ትጠጣላችሁ፤ ጥምቀቴንም ትጠመቃላችሁ፤ በቀኜና በግራዬ መቀመጥን ግን ከአባቴ ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ የምሰጥ እኔ አይደለሁም ” አላቸው።

[24] ዐሥሩም ሰምተው በሁለቱ ወንድማማቾች ላይ አዘኑ።

[25] ጌታችን ኢየሱስም ጠርቶ እንዲህ አላቸው ፥ “አሕዛብን መኳንንቶቻቸው እንዲገዙአቸው፥ ታላላቆቻቸውም እንዲሠለጥኑባቸው፤ አታውቁምን?

[26] በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ከእናንተ የበላይ ሊሆን የሚወድ አገልጋይ ይሁናችሁ።

[27] ከእናንተም አለቃ ሊሆን የሚወድ፥ ሎሌ ይሁናችሁ።

[28] የሰው ልጅ ሊያገለግል፥ ሰውነቱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣምና።”

[29] ከኢያሪኮም በወጣ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተከተሉት።

[30] እነሆ፥ ሁለት ዕውራን በመንገድ አጠገብ ተቀምጠው ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ሲያልፍ ሰምተው ፥ “አቤቱ፥ የዳዊት ልጅ፥ ይቅር በለን ” እያሉ ጮኹ።

[31] ሕዝቡ ግን ዝም እንዲሉ ይቈጡአቸው ነበር፤ እነርሱ ግን ፥ “አቤቱ፥ የዳዊት ልጅ፥ ማረን ” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

[32] ጌታችን ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና ፥ “ምን ላደርግላችሁ ትወዳላችሁ?” አላቸው።

[33] እነርሱም ፥ “አቤቱ፥ ዐይኖቻችን እንዲከፈቱ ነው ” አሉት።

[34] ጌታችን ኢየሱስም አዘነላቸው፤ ዐይኖቻቸውንም ዳሰሳቸው፤ ወዲያውም አዩና ተከተሉት።

የማቴዎስ ወንጌል። — Chapters