Skip to content
zeno
Create a Station
Explore
Podcasts
Audiobooks
Bible
By Genre
By Location
By Language
Religious
Music
News
Download App
Opens in a new window
Toggle Sidebar
zeno
DW | Amharic - News
Amharic
News, Analysis and Service from Germany and Europe - in 30 Languages
Website
Episodes
Episodes
13
13 October 2026
በአማራ ክልል በሶስት ዞኖች የሚደረገዉ ዉጊያ ቀጥሏል
ሌላው የወገልጤና ከተማ ነዋሪም ጦርነቱ በወገልጤና ከተማ ውስጥ መሆኑን ገልጸው ተዋጊዎቹ ማህበረሰቡን ከተማ ለቆ እንዲወጣ ጥሪ ማቀረባቸውን ይናገራሉ። ትናንት በመጀመርያው ጦርነትም በተባራሪ ጥይት የተመቱ ሰዎች መኖራቸውና ጉዳቱ ግን የከፋ አለመሆኑን ተናግረዋል።
13 October 2026
የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሥብሰባ ዉሳኔዎች
ፕረዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ዓርብ በማዕቀብ ውስጥ ካለችው ሩሲያ ናፍታ ለማስገባት ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር መስማምታቸውን ማስታወቃቸው ከዩክሬን ብቻ ሳይሆን ከህብረቱ አገሮችም ተቃውሞ የተሰማበት ሲሆን፤ ሚኒስትሮቹ ግን በስብሰባቸው በሩሲያ ላይ ይልቁንም ከፍተኛ የተባለውን የማዕቀብ ውሳኔ ያሳለፉ መሆኑን ውይዘሮ ካያ ካላይ አስታውቀዋል
13 October 2026
የዩናይትድ ስቴትስና ብሪታንያ ወደ ኢትዮጵያ ለሚጓዙ ዜጎቻቸዉ አዲስ ማሳሰቢያ አወጡ
ትናንት ባወጣው የጉዞ ማሳሰቢያ የተለያዩ ምንጮችን የጠቀሰው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የትግራይ የሰላም ኃይሎች ትግራይ ክልል ውስጥ አዲግራት፣ አድዋ እና ሽሬን ጨምሮ አቢ አዲ ከተሞችን መቆጣጠራቸውን፣ ከሰሜን አፋር አካባቢ የታጠቁ የተቃዋሚ ኃይሎችን ማስወገዳቸውንም አመልክቷል።
13 October 2026
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) «ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይገባል» አለ
“ቀይ ባህር ለዚህ አገር ህዝብ የተገባ ነው” የሚል ርዕስ ሰጥቶት ትናንት ባወጣው መግለጫ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦንግ)፤ “ኤርትራ እና ሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ (ህወሓት) የደርግ ወታደራዊ መንግስት ውድቀትን ተከትሎ በነበራቸው ስልታዊ የፖለቲካ ትስስር ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ላይ የባህር በር መውጫን ዘግተዋል” ሲል ተችቷል፡
13 October 2026
የፍልሰተኛችን ሞት ለመቀነስ መደበኛ መስመሮች እንዲስፋፉ አንድ ባለሙያ ጠየቁ
ከአፍሪካ ቀንድ ተነስቶና ቀይ ባህርን አቋርጦ ወደ የመን የሚዘልቀውና ምስራቃዊው የጉዞ መስመር የሚባለው የፍልሰተኛች መሄጃ አቅጣጫ እንኾ ገዳይነቱ ቀጥሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ እስካሁን 139 ሰዎች መሞታቸውን አለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት- አይአኤም አስታውቋል።
13 October 2026
የዓይን ጤና ንጽሕናውን ከመጠበቅ ይጀምራል
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ የዓይን ማዝ የበርካታ ሰዎች ዓይን የጤና ችግር እንደሆነ የዘርፉ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። የዓይን ንጽሕና በመጠበቅ እና በቀላል የህክምና እርዳታ ሊድን በሚችለው በዚህ የዓይን የጤና ችግር ብዙዎች የዓይን ብርሃናቸውን ሊያጡ ይችላሉ።
12 October 2026
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ መቆሚያዉ መቼ ነዉ?
የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ጠብ በናረበት በዚሕ ወቅት የኢትዮጵያ የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊ፣ሌሎች ባለሥልጣናት፣ የጦር ጄኔራሎችና የተባባሪዎቹ ኃይላት የጦር አዛዦች ሥልታዊቱን ከተማን አዲግራትን የመጎብኘታቸዉ ፖለቲካዊ መልዕክት ከደብረፂዮን እኩል ለኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑ ግልፅ ነዉ።
12 October 2026
ባለፉት ሦስት ሳምንታት ግድም በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭቶች ካገረሹ በኋላ በግጭቱ የሚከሰተው የሰብዓዊ ቀውስ በእጅጉ ስጋት ቀስቅሷል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ዳግም ያገረሸውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ከተሞች በፌፌራል የጸጥታ ሃይሎች ስር በገቡ ከተሞች ለኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት አመራሮች አቀባበል ተደርጓል፡፡ በትናንቱ የአመራሮች አቀባበል ወቅት በርካታ የማህበረሰብ አካላት ደስታቸውን ብገልጹም፤ ስጋቶችም ግን እስካሁን ሙሉ በሙሉ አለመወገዳቸው እየተነገረ ነው፡፡
11 October 2026
ትግራይ፦ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መፋለሚያ?
በትግራይ ክልል እየተደረገ የሚገኘው ውጊያ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ፍጥጫ ወደ ሌላ የግጭት ምዕራፍ ሊሸጋገር ዳር ዳር እያለ ነው። በመቶ ሺሕዎች የተገደሉባቸው ሁለት የጦርነት ታሪኮች ያላቸው አገራት ፍጥጫ ምን ያክል አስጊ ነው? ሦስት እንግዶች የተሳተፉበት ውይይት የውጊያውን አደጋ፤ ለሰላማዊ ሰዎች የሚያስከትከትለው መዘዝ ይፈትሻል።
10 October 2026
የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና መልስ የሚሻው የርዳታ አቅርቦት ፍላጎት
የተመድ ዋና ጸሐፊ በሰሜን ኢትዮጵያ ሶስት ክልሎች ዳግም የተቀሰቀሰው ግጭት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል