Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 3:16

[1] እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትኑሩ።

[2] እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፤ “ብትገዘሩም በክርስቶስ ዘንድ ምንም አይጠቅማችሁም።”

[3] ደግሞም ለተገዘረ ሰው ሁሉ የኦሪትን ሕግ መፈጸም እንደሚገባው እመሰክራለሁ።

[4] በኦሪት ልትጸድቁ የምትፈልጉ እናንተ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋዉ ወድቃችኋል።

[5] እኛ ግን በመንፈስ ቅዱስ፥ በእምነትም ልንጸድቅ ተስፋ እናደርጋለን።

[6] በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ በፍቅር የምትሠራ እምነት እንጂ መገዘር አይጠቅምምና፤ አለመገዘርም ግዳጅ አይፈጽምምና።

[7] ቀድሞስ በመልካም ተፋጥናችሁ ነበር፤ በእውነት እንዳታምኑ ማን አሰናከላችሁ?

[8] ይህ መፋጠናችሁ ከሚጠራችሁ አይደለምና።

[9] ጥቂት እርሾ ብዙውን ዱቄት መጻጻ ያደርገው የለምን?

[10] እኔ ሌላ እንዳታስቡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምኛችሁ ነበር፤ የሚያውካችሁ ግን የሆነው ቢሆን ፍዳውን ይሸከማል።

[11] ወንድሞቼ ሆይ፥ እኔ ግዝረትን ገና የምሰብክ ከሆነ፥ እንግዲህ ለምን ያሳድዱኛል? እንግዲህ የክርስቶስ የመስቀሉ ተግዳሮት እንዲያው ቀርቶአል።

[12] የሚያውኩአችሁም ሊለዩ ይገባል።

[13] ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተስ ለነጻነት ተጠርታችኋል፤ ነገር ግን በሥጋችሁ ፈቃድ ለነጻነታችሁ ምክንያት አታድርጉላት፤ ለወንድሞቻችሁም በፍቅር ተገዙ።

[14] “ወንድምህን እንደ ራስህ ውደድ ” የሚለው አንድ ቃል ሕግን ሁሉ ይፈጽማልና።

[15] እርስ በርሳችሁ የምትበላሉና የምትነካከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በርሳችሁ እንዳትተላለቁ ተጠንቀቁ።

[16] እላችኋለሁ፤ በመንፈስ ኑሩ እንጂ የሥጋችሁን ፈቃድ አታድርጉ።

[17] ሥጋ መንፈስ የማይሻውን ይሻልና፥ መንፈስም ሥጋ የማይሻውን ይሻልና፥ የምትሹትንም እንዳታደርጉ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ።

[18] የመንፈስን ፈቃድ የምትከተሉ ከሆናችሁ፥ ከኦሪት ወጥታችኋል።

[19] የሥጋም ሥራው ይታወቃል፤ እርሱም ዝሙት፥ ርኵuሰት፥ መዳራት፥

[20] ጣዖት ማምለክ፥ ሥራይ ማድረግ፥ መጣላት፥ ኵuራት፥ የምንዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቐጣ፥ ጥርጥር፥ ፉክክር፥ ምቀኝነት፥ መጋደል፥ ስካር ይህንም የመሰለ ሁሉ ነው።

[21] አስቀድሜ እንደ ነገርኋችሁ ይህን የሚያደርግ የእግዚአብሔርን መንግሥት አያይም።

[22] የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ምጿት፥ ቸርነት፥ እምነት፥ ገርነት፥ ንጽሕና ነው።

[23] ከዚህ ሕግ የሚበልጥ የለም።

[24] በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ግን ሰውነታቸውን ከምኟትና ከኀጢአት ለዩ።

[25] አሁንም በመንፈስ እንኑር፤ በመንፈስም እንመላለስ።

[26] ኩሩዎች አንሁን፤ እርስ በርሳችን አንተማማ፤ እርስ በርሳችንም አንቀናና።

ወደ ገላትያ ሰዎች። — Chapters