Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 2:22

[1] መንፈስ ፥ በኋላ ዘመን ብዙዎች ሃይማኖታቸውን እንደሚክዱ፥ የሚያስቱ አጋንንትንና የሰይጣናትን ትምህርትም እንደሚከተሉ በግልጥ ይናገራል።

[2] እነርሱም በግብዝነት ሐሰትን የሚናገሩ፥ በገዛ አሳባቸውም የሚቃጠሉ ናቸው።

[3] ጋብቻን እርም ይላሉ፤ እውነት የሚያውቁ ምእመናንም በልተው ያመሰግኑ ዘንድ እግዚአብሔር የፈጠራቸውን ምግቦች ይከለክላሉ።

[4] እግዚአብሔር የፈጠረው ፍጥረት ሁሉ መልካም ነውና፤ እያመሰገኑም ቢቀበሉት ምንም የሚጣል የለበትምና።

[5] በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት ይቀደሳልና።

[6] ይህንም ለወንድሞችህ አስተምራቸው፤ የሃይማኖትን ቃልና የተከተልኸውን መልካም ትምህርት እየመገብሃቸው፥ የተመረጠ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ትሆናለህ።

[7] ከረከሰ ጨዋታና ከባልቴቶች ተረት ግን ራቅ፤ ራስህንም ለመልካም አምልኮ አስገዛ።

[8] ለሥጋ መገዛት ለጥቂት ዘመን ይጠቅማል፤ መልካም አምልኮ ግን በሁሉ ግዳጅን ትፈጽማለች፤ በዚህ ዓለምና በሚመጣውም ዓለም የሕይወት ተስፋ አላት።

[9] ነገሩ የታመነ ነው፤ በሁሉም ሊቀበሉት ይገባል።

[10] ስለዚህ እንደክማለን፤ እንሰደባለንም፤ ሰውን ሁሉ፥ ይልቁንም የሚአምኑትን አዳኝ በሆነው በሕያው እግዚአብሔር ታምነናልና።

[11] ይህን እዘዝና አስተምር።

[12] በቃልና በኑሮ፥ በፍቅርም፥ በእምነትም፥ በንጽሕናም ለሚያምኑት ምሳሌ ሁን እንጂ ታናሽነትህን ማንም አይናቀው።

[13] እስክመጣ ድረስ በማንበብና በመምክር፥ በማስተማርና በመጸለይ ተጠንቀቅ።

[14] ትንቢት ከመናገር ጋር በጳጳሳት እጅ መጫን የተሰጠህን በአንተ ላይ ያለውን ጸጋ አታቃልል።

[15] ፍጹምነትህ በሁሉ ይታወቅ ዘንድ ይህን አንብብ፤ በዚህም ጸንተህ ኑር።

[16] እንግዲህ ለራስህና ለትምህርትህ ተጠንቀቅ፤ በእነዚህም ጸንተህ ኑር፤ ይህን ብታደርግ ራስህንም፥ የሚሰሙህንም ታድናለህና።

ወደ ጢሞቴዎስ። 1 — Chapters