Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 2:07

[1] ከሁሉ አስቀድሞ ጸሎትና ልመና፥ ምልጃና ምስጋናም ለሰዎች ሁሉ፥

[2] ለነገሥታትና ለመኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ እመክርሃለሁ፤ ይህም ኑሮአችን ፥ በቅንነት፥ በጸጥታና በርጋታ እንዲሆን ነው።

[3] ይህም በመድኀኒታችን በእግዚአብሔር ፊት መልካምና የተመረጠ ነው።

[4] ሰዎች ሁሉ ይድኑ ዘንድ፥ እውነትንም ያውቌት ዘንድ እርሱ ይወድዳልና።

[5] እግዚአብሔር አንድ ነው፤ በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛውም አንድ ነው፤ እርሱም ሰው የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

[6] ራሱንም ለሁሉ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤ በጊዜውም ምስክር ሆነ።

[7] እኔም ሐዋርያና ዐዋጅ ነጋሪ ሆኜ ተሾምሁለት፤ እውነትንም እናገራለሁ፤ አልዋሽምም፤ በእምነትና በእውነትም ለአሕዛብ መምህር ሆንሁ።

[8] እንግዲህ ወንዶች በስፍራው ሁሉ የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሡ፥ ያለ ቐጣና ያለ መጠራጠር እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ።

[9] እንዲሁም ሴቶች በሚገባ ልብስና በማፈር፥ በማስተዋልም፥ ራሳቸውንም ከዝሙት በማንጻት ለጸሎት ይዘጋጁ፥ በወርቅ ድሪና በዕንቐ፥ ዋጋው በከበረና ባማረ ልብስም አይደለም፤ ፀጕuራቸውንም በመሠራት አይደለም።

[10] እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሴቶች እንደሚገባ መልካም በመሥራት ነው እንጂ።

[11] ሴትም በጸጥታ ትማር፤ በፍጹም ቅንነትም ትታዘዝ።

[12] ሴት ግን በጸጥታ ትኑር እንጂ፥ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ እንድትሠለጥን አንፈቅድም።

[13] አዳም በፊት ተፈጥሮአልና፥ ከእርሱም በኋላ ሔዋን ተፈጠረች።

[14] አዳም አልሳተም፤ ነገር ግን ሴቲቱ ተሳሳተች፤ ትእዛዙንም ተላለፈች።

[15] ነገር ግን በእምነትና በፍቅር፥ በቅድስናም ራሳቸውንም በማንጻት ቢኖሩ በልጆችዋ ትድናለች።

ወደ ጢሞቴዎስ። 1 — Chapters