Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 2:42

[1] በእናንተ ዘንድ ጥልና መጋደል ከወዴት ይመጣሉ? በሰውነታችሁ ውስጥ የሚሠራውን ዝሙት ከመውደድ የተነሣ ከዚህ አይደለምን?

[2] ትመኛላችሁ እንጂ አታገኙም፤ ትቀናናላችሁ፤ ትገዳደላላችሁ፤ በብርቱም ትፈልጋላችሁ፤ ልታገኙም አትችሉም፤ ትጣላላችሁ፥ ቷጉማላችሁ፤ ነገር ግን አትለምኑምና የምትፈልጉትን አታገኙም፤

[3] ትለምናላችሁ፤ ለፍትወታችሁ ትከፍሉ ዘንድ ለክፉ ትለምናላችሁና አታገኙም።

[4] እናንተ ዘማውያን ሆይ፥ ይህን ዓለም የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት እንደ ሆነ አታውቁምን? የዚህን ዓለም ፍቅር የመረጠ ሰው የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናልና።

[5] ወይስ በእናንተ ላይ ያደረው መንፈስ መቃናትን እንደሚወድ መጽሐፍ በሐሰት የሚናገር ይመስላችኋልን?

[6] ነገር ግን ፈጣሪያችን የምትበልጠውን ጸጋ ይሰጣል፤ ስለዚህም “እግዚአብሔር ትዕቢተኟችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ” ይላል።

[7] እንግዲህ እግዚአብሔርን እሺ በሉት፤ ሰይጣንን ግን እንቢ በሉት፤ ከእናንተም ይሸሻል።

[8] እግዚአብሔርን ቅረቡት፤ ይቀርባችሁማል፤ እናንተ ኅ~ጥኣን እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት ዐሳብም ያላችሁ እናንተ ልባችሁን አጥሩ።

[9] እዘኑና አልቅሱ፤ ሳቃችሁን ወደ ልቅሶ፥ ደስታችሁንም ወደ ኀዘን መልሱ።

[10] በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ከፍ ያደርጋችኋል።

[11] ወንድሞቻችን ሆይ፥ እርስ በርሳችሁ አትተማሙ፤ ወንድሙን የሚያማ፥ የሚነቅፈውም የእግዚአብሔርን ሕግ ያማልና፤ የእግዚአብሔርንም ሕግ ይነቅፋልና፤ ሕጉን የምትነቅፍ ከሆንህ ደግሞ፥ ሕግ አፍራሽ ሆንህ እንጂ፥ ሕግን ፈጻሚ አይደለህም።

[12] ሕግን የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ነውና፤ ማዳንም፥ መግደልም የሚቻለው እርሱ ነው፤ እንግዲህ በሌላው የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?

[13] “ዛሬ፥ ወይም ነገ ወደዚያች ከተማ እንሄዳለን፤ በዚያችም ዓመት እንኖራለን፤ እንነግዳለንም፤ እናተርፋለንም ” የምትሉ እናንተ ተመልከቱ፤

[14] ነገ የሚሆነውን አታውቁምና፥ ሕይወታችሁ ምንድነው? እናንተማ ላንድ ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንደ ጢስ አይደላችሁምን?

[15] በዚህ ፈንታ “እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።”

[16] አሁን እናንተ በሥራችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚች ያለችው ትምክሕትም ኋላ ክፉ ናት።

[17] በጎ ነገር ማድረግን የሚያውቅ፥ የማይሠራትም ኀጢአት ትሆንበታለች።

የያዕቆብ መልእክት። — Chapters