Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 3:31

[1] ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ በአለበት በላይ ያለውን ሹ።

[2] የላይኛውን አስቡ፤ በምድር ያለውንም አይደለም።

[3] እናንተ ፈጽማችሁ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋራ በእግዚአብሔር ዘንድ የተሠወረች ናትና።

[4] ሕይወታችሁ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ ያንጊዜ ከእርሱ ጋር በፍጹም ክብር ትገለጣላችሁ።

[5] ምድራዊ ሰውነታችሁንም ከዝሙትና ከርኵuሰት፥ ከጥፋትና ከክፉ ምኟት፥ ጣዖት ማምለክ ከሆነው ከቅሚያም ግደሉት።

[6] በእነርሱም ምክንያት በማይታዘዙ ልጆች ላይ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ይመጣል።

[7] እናንተም ቀድሞ በዚህ ሥራ በነበራችሁ ጊዜ የሄዳችሁበት ነው።

[8] አሁንም ቐጣንና ብስጭትን፥ ክፋትንና ስድብን፥ የሚያሳፍረውንም ነገር ተዉ፤ ከንቱ ነገርም ከአፋችሁ አይውጣ።

[9] አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ተዉት እንጂ፤ ወንድሞቻችሁን አቷሹ።

[10] ፈጣሪውን ለመምሰል በዕውቀት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ልበሱት።

[11] በእርሱ ዘንድ አይሁዳዊ፥ ግሪካዊም፥ የተገዘረ፥ ያልተገዘረም፥ አረመኔም፥ ባላገርም፥ ቤተ ሰብእና አሳዳሪ ማለት የለም ነገር ግን ክርስቶስ ለሁሉ በሁሉም ዘንድ ነው።

[12] እንግዲህ እግዚአብሔር እንደ መረጣቸው ቅዱሳንና ወዳጆች፥ ምሕረትንና ርኅራኄን፥ ቸርነትንና ትሕትናን፥ የውሀትንና ትዕግሥትን ልበሱት።

[13] ባልንጀሮቻችሁን ታገሡአቸው፤ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ፤ ባልንጀሮቻችሁን የነቀፋችሁበትን ሥራ ተዉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።

[14] ከዚህም ሁሉ ጋር ዘወትር ተፋቀሩ፤ የመጨረሻው ማሰሪያ እርሱ ነውና።

[15] በአንድ አካል የተጠራችሁለት የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ጸንቶ ይኑር፤ ክርስቶስንም በማመስገን ኑሩ።

[16] በጥበብ ሁሉ እንድትበለጽጉ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ዘንድ ይጽና፤ በመንፈስም ራሳችሁን አስተምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝሙርንና ምስጋናን፥ የቅድስና ማሕሌትንም በልባችሁ በጸጋ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።

[17] በቃልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ፤ ስለ እርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑት።

[18] ሚስቶች ሆይ ለእግዚአብሔር እንደምትታዘዙ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።

[19] ባሎች ሆይ ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ አትንቀፉአቸውም።

[20] ልጆች ሆይ ለወላጆቻችሁ በሁሉ ታዘዙ፤ እንዲህ ማድረግ ይገባልና፤ ይህም እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛልና።

[21] አባቶች ሆይ እንዳያዝኑ ልጆቻችሁን አታበሳጩ።

[22] አገልጋዮች ሆይ በቅን ልብ እግዚአብሔርን በመፍራት እንጂ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፥ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ።

[23] ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ የምታደርጉትን ሁሉ ከልብ አድርጉት።

[24] ከእግዚአብሔር ዋጋችሁን እንደምትቀበሉ ታውቃላችሁ፤ ለክርስቶስ ትገዛላችሁና፤

[25] የሚበድል ግን ፍዳውን ያገኛል፤ እርሱም አያደላለትም።

ወደ ቈላስይስ ሰዎች። — Chapters