Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 2:43

[1] ነገር ግን በኋላ ዘመን ክፉ ጊዜ እንደሚመጣ ይህን ዕወቅ።

[2] ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፥ ገንዘብንም የሚወዱ፥ ቀባጣሪዎች፥ ትምክሕተኟች፥ ትዕቢተኟች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ ምስጋና የሌላቸው፥ ከጽድቅም የወጡ ይሆናሉ።

[3] ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኟች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኟች፥ መልካም የሆነውንም የሚጠሉ ይሆናሉ።

[4] ከዳተኟች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚመርጡ ይሆናሉ።

[5] የአምልኮት መልክ አላቸው፤ ኀይሉን ግን ይክዱታል፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ራቃቸው።

[6] እነዚህ በየሰው ቤት የሚገቡና በኀጢአት የተተበተቡትን ሴቶች የሚማርኩ፥ ወደ ብዙ ምኟትም የሚደርሱ ናቸውና፤

[7] ዘወትር ይማራሉ፤ ነገር ግን እውነትን ከቶ አያውቌትም።

[8] ኢያኔስና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደ ተቃወሙት እነዚህም እውነትን ይቃውሙአታል፤ አእምሮአቸውም የጠፋባቸውና ከእምነት የወጡ ሰዎች ናቸው።

[9] ነገር ግን ከፍ ከፍ አይሉም፤ የእነዚያ ስንፍና ደግሞ እንደ ተገለጠ ስንፍናቸው በዝታ ለሁሉም ተገልጣለችና።

[10] አንተ ግን ትምህርቴንና ግብሬን፥ አሳቤንም፥ እምነቴንም፥ ትዕግሥቴንም፥ ፍቅሬንም፥ መጽናናቴንም ተከተልህ፤

[11] ስደቴንና፥ መከራዬንም ተከተልህ፤ በአንጿኪያና በኢቆንዮን፥ በልስጥራንም ያገኘኝን የታገሥሁትንም ስደት ታውቃለህ፤ ከሁሉም እግዚአብሔር አዳነኝ።

[12] ኢየሱስ ክርስቶስንም በማምለክ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።

[13] ነገር ግን ክፉዎች ሰዎችና አታላዮች በክፋት ላይ ክፋትን እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ ራሳቸው ይስታሉ፤ ሌላውንም ያስታሉ።

[14] አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ጸንተህ ኑር፤ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና።

[15] ከሕፃንነትህም ጀምረህ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን ዐውቀሃል።

[16] በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ ሁሉ ለፍጹም ትምህርትና ለተግሣጽ፥ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ጥበብ ይጠቅማል።

[17] የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ምግባር ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ።

ወደ ጢሞቴዎስ 2 — Chapters