Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 4:56

[1] የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ከሚሆን ከያዕቆብ ወንድም ከይሁዳ፥ እግዚአብሔር አብ ለሚወዳቸው በኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፥

[2] ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።

[3] ወንድሞቻችን ሆይ፥ ስለ ሁላችን መዳን እጽፍላችሁ ዘንድ በሁሉ ተፋጠንሁ፤ እጅግ ተግቼ እጽፍላችኋለሁና፥ ለቅዱሳን የተሰጠችውንም ሃይማኖት ትጋደሉላት ዘንድ እማልዳችኋለሁ።

[4] አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ በደለኟች ሰዎች ተቀላቅለውባችኋልና፤ እነርሱም እግዚአብሔርን የማይፈሩና የእግዚአብሔርን ጸጋ ወደ ዝሙታቸው የሚለውጡ፥ ብቻውን ንጉሥ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም የሚክዱ ናቸው።

[5] ሁሉንም አሳስባችሁ ዘንድ ወደድሁ፤ ጌታ አንድ ጊዜ ሕዝቡን ከምድረ ግብፅ እንደ አዳነ፥ በሁለተኛም ጊዜ ያላመኑትን እንደ አጠፋቸው ታውቃላችሁ።

[6] መኖሪያቸውን የተዉትን፥ የራሳቸውንም አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘለዓለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ ጠብቌቸዋል።

[7] እንደዚሁም ሰዶምና ገሞራ፥ በዙሪያቸውም የነበሩ ከተሞች፥ ለዝሙትና ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጭ ለሆነ ሩካቤ ሥጋ ራሳቸውን አሳልፈው ስለ ሰጡ፥ በዘለዓለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል።

[8] እንዲሁም እነዚህ ሰዎች ደግሞ በሕልማቸው ሥጋቸውን ያረክሳሉ፤ ጌታቸውንም ይክዳሉ፤ ክብሩንም ይሰድባሉ።

[9] የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳን ስለ ሙሴ ሥጋ ከሰይጣን ጋር በተከራከረ ጊዜ የስድብ ቃልን ሊናገር አልደፈረም፤ “እግዚአብሔር ይገሥጽህ ” አለው እንጂ።

[10] እነዚህ ግን የማያውቁትን በመሳደብ ይበድላሉ፤ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ።

[11] ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና፤ በበለዓም የዐመፅ ዋጋም ተቃጥለዋልና፤ በቆሬና በወገኖቹም ክሕደት ጠፍተዋል።

[12] እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ፥ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኟች ያለ ፍርሀት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ፥ ውኃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ፥ ሁለት ጊዜ የሞቱ፥ ከነሥራቸው የተነቀሉ፥ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥

[13] የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተጠበቀላቸው፥ የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።

[14] ከአዳም ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ፥ ስለ እነርሱ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ ፥ “እነሆ እግዚአብሔር በሁሉ ላይ ይፈርድ ዘንድ ከአእላፋት ቅዱሳን መላእክት ጋር ይመጣል።

[15] ኃጥኣንን ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ሥራ ሁሉ፥ ከዳተኟችንና ኀጢኣተኟችንም የማይገባውን ቃል ሁሉ በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ይዘልፋቸዋል።”

[16] እነዚህ እንደ ምኟታቸው እየሄዱ፥ የሚያንጐራጕuሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕuረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ትዕቢትን ይናገራል።

[17] ወንድሞቻችን ሆይ፥ እናንተስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት መጀመሪያ ያስተማሩአችሁን ቃል ዐስቡ።

[18] በኋላ ዘመን ልቡናቸው የወደደውን የሚያስተምሩና በእነርሱ ኀጢአት ሌላውን የሚያስቱ ዘባቾች እንደሚመጡ ነግረዋችኋልና።

[19] በኀጢአታቸው የሚለያዩና ልቡናቸው በወደደው የሚያስቱ፥ መንፈስ ቅዱስም ያላደረባቸው እነዚህ ናቸው።

[20] ወንድሞቻችን ሆይ፥ እናንተ ግን በተቀደሰች ሃይማኖት ራሳችሁን እነጹ፤ በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ።

[21] በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ፤ ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስንም ምሕረት ተስፋ አድርጉ።

[22] በኀጢአቱ ምክንያት የምትዘልፉት አለ፤ የምትምሩትም አለ።

[23] ከእሳት የምታድኑትና የምትታደጉት አለ፤ ፈርቶና ተጸጽቶም የሚድን አለ፤ የቀደመ በደላቸውንም ጠልተው የዝሙት ርኵuሰት ልብሳቸውን የጣሉ አሉ።

[24] ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌለባችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው፥

[25] ብቻውን ለሆነ መድኀኒታችን እግዚአብሔር ከዘመን ሁሉ በፊት፥ አሁንም እስከ ዘለዓለም ድረስ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ፥ ኀይልም፥ ሥልጣንም ይሁን። አሜን። የያዕቆብ ወንድም የሐዋርያው የቅዱስ ይሁዳ መልእክት ተፈጸመች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘለዓለም። አሜን።