Skip to content
Opens in a new window
Listen to this chapter • 4:35

[1] እንግዲህ ክፋትን ሁሉ፥ ሐሰት መናገርንም ሁሉ፥ ጥርጥርንም፥ መተማማትንም፥ መቃናትንም ከእናንተ አርቁ።

[2] ዛሬ እንደ ተወለዱ ሕፃናትም ሁኑ፤ ለመዳን በእርሱ ታድጉ ዘንድ ቅልቅል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።

[3] እነሆ፥ እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቀምሳችኋል።

[4] በሰውም ወደ ተናቀ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ ቅረቡ።

[5] ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

[6] እንዲህ ተጽፎአልና “እነሆ በጽዮን የተመረጠውንና የከበረውን የማእዝን ድንጋይ አኖራለሁ፤ በእርሱ ያመነም አያፍርም።”

[7] ለምታምኑ ለእናንተ ክብር ነው፤ ለሚክዱት ግን “አናጢዎች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዝን ራስ ሆነ።”

[8] እርሱም በቃሉ ለሚጠራጠሩና የተፈጠሩበትን ለሚክዱ የዕንቅፋት ድንጋይና የማሰናከያ ዐለት ነው።

[9] እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትነግሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የመንግሥትና የክህነት ወገን፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱም የተለየ ወገን ናችሁ። ቲቶ

[10] እናንተ ቀድሞ ወገኖቹ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገኖች ናችሁ፤ እናንተ ምሕረትን ያገኛችሁ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

[11] የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ከሥጋዊ ምኟት ትርቁ ዘንድ፥ እንግዶችና መጻተኟች፥ ደካሞችም እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ።

[12] ስለሚመለከቱት ስለ መልካሙ ሥራችሁ ክፉ እንደምታደርጉ፥ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር በሚጐበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል አካሄዳችሁ መልካም ይሁን።

[13] ለእግዚአብሔር ብላችሁ ለሰው ሁሉ ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤

[14] ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ አድራጊዎችን ሊቀጡ፥ በጎ አድራጊዎችንም ሊያመሰግኑ እርሱ ይልካቸዋልና።

[15] በመልካሙ ሥራችሁ፥ እግዚአብሔርን የማያውቁትን የሰነፎች ሰዎችን አፍ ዝም ታሰኙ ዘንድ፥ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና።

[16] ነጻነት ወጥታችሁ፥ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።

[17] ሁሉን አክብሩ፤ ባልንጀራችሁንም ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩት፤ ንጉሥንም አክብሩት።

[18] እናንተ ሎሌዎችም እየፈራችሁ፥ ለጌቶቻችሁ ተገዙ፤ ለክፉዎችም እንጂ ለደጎችና ለሚራሩት ብቻ አይደለም።

[19] በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኀዘንን ቢታገሥ ጸጋን ያገኛልና።

[20] በድላችሁ የመጣባችሁን ብትታገሡ፥ ምስጋናችሁ ምንድን ነው? ነገር ግን መልካም እየሠራችሁ፥ የደረሰባችሁን ግፍ ብትታገሡ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የምታስመሰግን ይህቺ ናት።

[21] ለዚህ ተጠርታችኋልና፤ ክርስቶስም እኮ ፍለጋውን ትከተሉ ዘንድ ምሳሌውን ሊተውላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአል።

[22] እርሱ ኀጢአት አልሠራም፤ በአንደበቱም ሐሰት አልተገኘበትም።

[23] ሲሰድቡት አልተሳደበም፤ መከራ ሲያጸኑበትም አልተቀየመም፤ ነገር ግን እውነተኛ ፍርድን ለሚፈርደው አሳልፎ ሰጠ።

[24] ከኀጢአታችን ያወጣን ዘንድ፥ በጽድቁም ያድነን ዘንድ፥ እርሱ ስለ ኀጢአታችን በሥጋው በእንጨት ላይ ተሰቀለ፤ በግርፋቱም ቐስል ቐስላችሁን ተፈወሳችሁ።

[25] እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፤ አሁንም ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመለሱ።

የጴጥሮስ መልእክት። — Chapters