የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የተጣለበት ተስፋ እና የተገተረው ድርድር
07 September 2025

የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የተጣለበት ተስፋ እና የተገተረው ድርድር

እንወያይ | Deutsche Welle

About
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ጉባ ወረዳ መጋቢት 24 ቀን 2003 ግንባታው የተጀመረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ተጠናቆ በመጪው ማክሰኞ ይመረቃል። ኢትዮጵያ ከሱዳን ከምትዋሰንበት ድንበር በ30 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የሚገኘው ግድብ የግንባታ ሒደቱ 14 ዓመታት ገደማ የወሰደ ነው። የኃይል ማመንጫው 13 ተርባይኖች ተገጥመውለታል። በግድቡ የተገጠሙ ተርባይኖች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ በድምሩ 5,150 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫሉ። በግድቡ የተፈጠረው ሰው ሠራሽ ኃይቅ 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ይይዛል። ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው፤ ኢንጂነር አሥራት ብርሀኑ እና ወንድወሰን ሚቻጎን ስለ ታሪካዊው ምዕራፍ አወያይተናል።