
About
1983 ወታደራዊ ሥርዓት ተወገደ።ኤርትራ ነፃ ወጣች።በ1960ዎቹ መልስ አላገኘም የተባለዉ የብሔር-ብሔረሰቦች ጥያቄ መልስ አገኘ ተባለ።በጎሳ ላይ የተመሠረተ ፈ,ደራሊዝም መመሥረቱም ታዋጀ።ጦርነቱ ግን ቀጠለ።ክፍፍሉም ከብሔሮች ወይም ጎሳዎች አልፎ ወደ ንዑስ-ብሔሮች፣ ከዚያም እስከ ጎጥ ቀጥሎ ዛሬ ያንድ ብሔር ወይም ጎሳ አባላት የሆኑ የማሕበረሰብ ክፍሎች እየተቧደኑ ወይም በተናጥል ይጋጫሉ፣ ይገዳደላሉም።