ማሕደረ ዜና ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን የዉጊያ ሥልትና መልስ የለሽ ጥያቄዎች
16 March 2026

ማሕደረ ዜና ፣ የእስራኤል-ዩናይትድ ስቴትስና የኢራን የዉጊያ ሥልትና መልስ የለሽ ጥያቄዎች

ማሕደረ ዜና

About
የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መንግሥት ኃይለማርያም የናደዉ ዕዝ በ1987 (እጎአ መሆኑን አይዘንጉ) ግድም አፍአበት ላይ የገጠመዉን ሽንፈት ጠላት «አካቢዉን ከበቦ ሲያበቃ የዕዙን ጭንቅላት በጠበጠዉ» ዓይነት ብለዉ ባጭሩ ገልፀዉት ነበር።የእስራኤልና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር የካቲት 28 ጧት የኢራንን የፖለቲካ፣ የጦርና የስለላ እናትን ቆርጦ ቢጥልም ፋርሶች እንደታሰበዉ «ያልተበጠበጡበት» ሁለተኛዉ ምክንያት የጠላታቸዉን የዉጊያ ሥልት ብዙ አጥንተዉ በቅርብ አመታት ኢራቅ፣ አፍቃኒስታንና ሊቢያ ላይ ከሆነዉ ተምረዉ የነኬይን ዘመናይ ሥልት በነ አፄ ምኒልክ ጥንታዊ ሥልት ለመመከት በመዘጋጀታቸዉ ነዉ።