Skip to content
zeno
Create a Station
Explore
Podcasts
Audiobooks
Bible
By Genre
By Location
By Language
Religious
Music
News
Download App
Opens in a new window
Toggle Sidebar
zeno
DW
ማሕደረ ዜና
Politics
Documentary
Amharic
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ
Website
Episodes
Episodes
100
12 October 2026
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ መቆሚያዉ መቼ ነዉ?
የኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ጠብ በናረበት በዚሕ ወቅት የኢትዮጵያ የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊ፣ሌሎች ባለሥልጣናት፣ የጦር ጄኔራሎችና የተባባሪዎቹ ኃይላት የጦር አዛዦች ሥልታዊቱን ከተማን አዲግራትን የመጎብኘታቸዉ ፖለቲካዊ መልዕክት ከደብረፂዮን እኩል ለኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑ ግልፅ ነዉ።
14 min
05 October 2026
ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦር መቀሌን ተቆጣጠረ፣ጦርነቱ አላባራም፣አካባቢያዊዉን ማስጋቱም ቀጥሏል
ከየካቲት 1981 ጀምሮ መቀሌ ከህወሓት እጅ ስትወጣ ያሁኑ ሁለተኛዋ ነዉ።የመጀመሪያዉ የፌደራሉ መንግሥት ህዳር 2013 ከተማይቱን ሲቆጣጠር ነበር።ግን ከሰባት ወር በላይ አልቆየም።ህወሓት መልሶ ተቆጣጠራት።ዘንድሮም ከመቀሌ ድል-ሽንፈት በኋላ ጦርነቱ ቦታ-ይቀይር እንጂ አላባራም
14 min
28 September 2026
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያ የጦርነት ማግሥት አዲስ ጦርነት መፍለቂያ ምድር
ጦርነት ሲጀመር «ተፋላሚዎች መጀመሪያ የሚገድሉት ዕዉነትን ነዉ» እንዲሉ ሆኖ የጦርነቱ ጀማሪ ማንነትን መለየት፣ እስካሁን የተገደለና የሞተዉን ሰዉ ቁጥር በዝርዝር ማወቅ አይቻልም።ተፋላሚ ኃይላት፣ ደጋፊዎቻዉ፣ መገናኛ ዘዴዎቻቸዉና በየፊናቸዉ ያደራጁት የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የፕሮፓጋንዳ ሠራዊ የሚነዙት የሐሰት መረጃ፣ስድብና ነቀፋም ቀጥሏል።
15 min
21 September 2026
ሑቲዎች እና ሳዑዲ አረቢያ የገጠሙት ጦርነት በደሐዋ የመን ሲቪሎችን ወደ ሰቆቃ እየገፋ ነው
የአንሳር አላሕ ንቅናቄ ከጅቡቲ 20 ኪሎ ሜትር ገደማ የምትርቀውን ማዩን ወይም ፔሪም ደሴት እና ኤርትራ ከየመን የተዋጋችባቸው የሐኒሽ ደሴቶችን ጨምሮ ከቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘውን ምዕራባዊ የመን ለመቆጣጠር የፈጀበት ሣምንት ገደማ ብቻ ነው። በውጊያው ቱርክ እና ፓኪስታን ሳዑዲ አረቢያን ለመደገፍ ፈቃደኛ ቢሆኑም አሜሪካ ለጊዜው ቸልተኛ ሆናለች።
12 min
14 September 2026
ማሕደረ ዜና፣ የመስከረም 11፣ 2001 ጥቃት ዝክር-«ጦርነቱ ይቀጥላል» ትራምፕ
ጥቃቱ ሲፈፀም ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ሳራሶታ፣ ፍሎሪዳ የአንድ ትምሕርት ቤት ተማሪዎችን እያነጋገሩ ነበር።ፕሬዝደንቱ ከመሩት የመልዕክተኞች ጓድ ጋር አብሮ የተጓዘዉ ጋዜጠኛ ስቲቭ ሆላንድ እንደሚያስታዉሰዉ ቡሽ ከኒዮርኩ ሕንፃዎች የመጀመሪያዉ መመታቱን ሲሰሙ «የፓይለት ስሕተት ነዉ» ብለዉ ነበር።ሁለተኛዉ መደገሙ ሲነገራቸዉ ግን ፊታቸዉ ተለዋወጠ።
14 min
07 September 2026
የጀርመንዋ ዛክሲሶንያ ግዛት ምርጫ ዉጤት በአዉሮጳ ፖለቲካ ላይ ያለዉ አንድምታ
12 min
31 August 2026
ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የእስራኤል መሪዎች የጫሩት ጦርነት 6ኛ ወር
በጣም ከረዘመ በሥድት ሳምንት የቴሕራን ሥርዓትን መነቃቅሮ ለመጣል፣ የኑክሌር መርሐ-ግብሯን ለመረከብና የአሜሪካ ታማኝ ሥርዓት ቴሕራን ላይ ለመትከል የዋሽግተን-ቴል አቪቭ መሪዎች ለየሕዝባቸዉ የገቡት ቃል ግን በርግጥ በንኗል
14 min
24 August 2026
ማሕደረ ዜና፣ የ4 ዓመታት ዝግጅት፣የ40 ቀናት ጉባኤ-ለኢትዮጵያ ይበጅ ይሆን?
ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተጠናቀቀዉ ምክክርም ህወሓትን ይዞ፣ ፋኖን፣ ኦነሠን፣ የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ክልሎች አማፂያንን አክሎ፣ ገሚስ-ኦብነግን፣ እንደ ኦነግ፣ ኦፌኮ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ከሐገር ዉጪ የሚገኙ የፖለቲካ፣ የአካባቢ፣ የመብት ተሟጋቻች ማሕበራትን ጨምሮ አራት አመታት በፈጀዉ የምክክር ሒደት አልተካፈሉም
21 min
17 August 2026
ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ እብሪት፣ በፍርሐት የተጠፈነገዉ ዓለምና የአፍሪቃ ፈተና
የሆርሙዝ ወሽመጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ በተለይ አፍሪቃ በማታዉቀዉ፣በማያገባትና በማትፈልገዉ ጦርነት የርዳታ ተመፅዋች ዜጎችዋን ሕይወት እንድትከፍል አስገድዷታል።ከኢትዮጵያ እስከ ናጄሪያ፣ ከሶማሊያ እስከ ሴኔጋል የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የርዳታ እሕል፣ መድሐኒት፣ቁሳቁስ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦባቸዋል
14 min
10 August 2026
ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙ
አፍሪቃ «የራስዋን ችግር በራስዋ መፍታት የመቻሏ» አብነት፣ ኢትዮጵያዉያን እንደሚዋጉት ሁሉ «ለሰላማዊ ዉል ለመገዛትም ፈቃደኛ የመሆናቸዉ» ምሳሌ ተደርጎ ብዙ የተነገረለት የፕሪቶሪያ ሥምምነት ተኩስ ከማስቆሙ እኩል የአዲስ የኃይል አሰላለፍ ምክንያት መሆኑ ነዉ ዚቁ።የተፋላሚ ኃይላት ዋና ተዋኞች በሥምምነቱ ይዘት፣አተረጓጎምና ገቢራዊቱ ላይ ከመነጋገር፣ ለመግባባት ከመጣር ይልቅ አጋር ፍለጋ ሲቃትቱ ከሶስት ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል።
13 min