
About
ሳዳም ሁሴይ፣ ኦስማ ቢን ላደን፣ ሙዓመር ቃዛፊ፣ ዑስማኢል ሐንያሕ፣ ሐሰን ነስረላሕ ሌሎችም ሲገደሉ ዓለም ከአምባገነኖች፣ከጨቋኞች እና ካሸባሪዎች መላቀቋን የቴል አቪቭ-ዋሽግተን-ለንደን-ብራስልስ መሪዎች ለዓለም አዉጀዉ ነበር።ዓለም ግን ዘንድሮም ሰላም አታዉቅም።አምና ጥር ለሁለተኛ ጊዜ የዩናይትድ ስቴትስን የፕሬዝደትነት ሥልጣን የያዙት ዶናልድ ትራምፕ የሰላም ፕሬዝደንት መሆናቸዉን ሲደሰኩሩ የልዕለ ኃያሊቱ ሐገር መሪዎች የጦርነትን አትራፊነት ብቻ ሳይሆን አስከፊነትቱን የተረዱ መስለዉ ነበር