About
Amharique - "Jésus est mort pour nous".mp3 / Amharic - "Jesus Died for Us".mp3 //
ዮሐንስ 1 - ቃል ሥጋ ሆነ1በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። 2እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ። 3ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። 4ሕይወት በእርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች። 5ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማውም አላሸነፈውም። 1፥5 ወይም ጨለማው ግን አላወቀውም6ከእግዚአብሔር የተላከ ዮሐንስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ። 7ሰዎች ሁሉ በእርሱ በኩል እንዲያምኑ፣ ስለ ብርሃን ምስክር ሆኖ ለመቆም መጣ፤ 8ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ እርሱ ራሱ ብርሃን አልነበረም። 9ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጪ የሆነው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር። 1፥9 ወይም ይህ ወደ ዓለም ለሚመጣ ሰው ብርሃን የሚሰጥ እውነተኛው ብርሃን ነበረ 10እርሱ በዓለም ውስጥ ነበረ፤ ዓለም የተፈጠረው በእርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ዓለም አላወቀውም። 11ወደ ራሱ ወገኖች መጣ፤ የገዛ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤ 12ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው። 13እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም 1፥13 ወይም ከሰው ውሳኔ ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።14ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም አደረ፤ እኛም ጸጋንና እውነትን ተሞልቶ ከአባቱ ዘንድ የመጣውን የአንድያ
1፥14 ወይም አንድ ልጁ የሆነው ልጅን ክብር አየን። 15ዮሐንስም፣ “ ‘ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይልቃል’ ብዬ የመሰከርሁለት እርሱ ነው” በማለት ጮኾ ስለ እርሱ መሰከረ። 16ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀብለናል፤ 17ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል መጣ። 18ከቶውንም እግዚአብሔርን ያየ ማንም የለም፤ ነገር ግን በአብ እቅፍ ያለው አንድያ ልጁ 1፥18 አንዳንድ ቅጆች አንድ ልጁ ይላሉ የሆነው አምላክ እርሱ ገለጠው።