የሀገር ግንባታ ደንቃራዎች26 October 2022በኢትዮጵያ የሀገረ መንግስት ግንባታ (State-building) ያለቀ ጉዳይ ነው፤ ነገር ግን የሀገር ግንባታ (Nation-building) ከጫፍ መድረሰ አልቻለም ይላሉ በቅርቡ በጉዳዩ ላይ መፅሀፍ ለንባብ ያቀረቡት አንተነህ ሙሉ። የሀገር ግንባታ ደንቃራዎች ምንድ ናቸው? የዋዜማው ብስራት ከፈለኝ መፅሐፉን ተመልክቶ ምሁሩንም አነጋግሯል። አድምጡት00:12:11
የደህንነቱ ሰውዬ14 September 2022የደህንነት ተቋምን ብቁ ለማድረግና የሀገርን ጥቅም ለማስጠበቅ የገጠሙን ፈተናዎች ምን ይመስላሉ። በተቋሙ በከፍተኛ ሃላፊነት ያገለገሉት በላይ ገብረፃድቅን አነጋግረናቸዋል። 00:14:52
መንግስት የውጪ ባንኮች ለምን ማስገባት ፈለገ?01 April 2022የውጪ ሀገር ባንኮች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ ለመፍቀድ በተያዘው ዕቅድ ላይ በመንግስትም ሆነ በባለሙያዎች ዘንድ መግባባት የለም። ይህ ብስራት ከፈለኝ ያዘጋጀው የዋዜማ ዘገባ በጉዳዩ ላይ የሚነሱ ክርክሮችን ተመልክቷል። አድምጡት00:16:40
ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ለመግዛት ጠይቃ የቁስል መሸፈኛ ፕላስተር ተልኮላታል28 February 2022ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ለመግዛት ጠይቃ የቁስል መሸፈኛ ፕላስተር ተልኮላታል። ይህ የዋዜማ ዘገባ የጦር መሳሪያ ግዥ ዲፕሎማሲን በተመለከተ ያሉብንን ፈተናዎች ያነሳል።00:17:26