ወደ እግዚአብሔር መመልከት
10 May 2021

ወደ እግዚአብሔር መመልከት

For Training Use

About
አይኖቻችን ያሉበት ህይወታችንን ይወስናል:: በየትኛውም ችግርና ፈተና ውስጥ ብንሆን አይኖቻችን ተከፍተው ጌታን ስናይ ፍፁም ለውጥ ይሆናል:: ነገሮቻችን ባይለወጡ እንኳ የኛ መለወጥ ግን እርግጥ ነው:: እግዚአብሔርን ማየት ሁለንተናን ይፈውሳል:: ከክፉዉ ዘመንና ጥፋቱ ማምለጫው ይኸው ነው:: ጌታን ማየት::
ጌታን ስናይ መፅናናት ሰላምና እረፍት ይሆንልናል:: በምንሰማውና በምናየው አንናወጥም አነደነግጥምም ይልቁን ምስጋናና ምህረት ባርኮትም ይበዛልናል:: እረጅም መንገድ የመጓዛችንም ሀቅም አይኖቻችን በጌታ ላይ በተተሉበት መጠን ልክ ነውና: አይኖቻችን ማንንና ምን ላይ እንደሆነ ራሳችንን ልንጠይቅ ያስፈልጋል