“ያነበባችሁትን ሰምተናል፤ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት … የኢትዮጵያን ታሪክ ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል፤ አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ‹አሁን ተራው የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ!”
ንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም፤ ከ 49 ዓመታት በፊት በዛሬው ዕለት ነው፤ በጽ/ቤታቸውም ሳሉ የተናገሯቸው የመጨረሻ ቃላት እኚህ ነበሩ፣ በእርግጥ ንግስናቸውን አስረክበውም ቢሆን በቤተመንግስቱ መቆየት ይችሉ እንደሁም ለ13ቱ የደርጉ ተወካዮች ጥያቄ ማቅረባቸውም በታሪክ ድርሳናት ሰፍሯል።