Skip to content
Opens in a new window
Endod Plus እንዶድ+
Endod Plus እንዶድ+
Mekonnen Mogessie

Endod Plus እንዶድ+

እንዶድ በእድገት፣ በተሞክሮ እና በአበርክቶት ሚዛን "ከ'ኛው ለ'ኛው!" ወደ ህይወት የበለጠ የሚያቀርቡን ሸጋ ጥያቄዎች የተሰተሩበት የራድዮ መሰናዶ ነው!

Episodes

"ሒዱ፤ መጣን!" ፲፮ - "ማሕበራዊ 'ሚዲያ' እና የሰብዕና ንቃቃቶቻችን"... 
10 October 2023

"ሒዱ፤ መጣን!" ፲፮ - "ማሕበራዊ 'ሚዲያ' እና የሰብዕና ንቃቃቶቻችን"... 

ምዕራፍ ፫ - "እኛ..." ቀዳሚ ተከታታይ መሰናዶ - "ሒዱ፤ መጣን!" ሶስተኛ ንዑስ ተከታታይ መሰናዶ - "ማንነት ከነቃ..." ክፍል ፲፮ - "ማሕበራዊ 'ሚዲያ' እና የሰብዕና ንቃቃቶቻችን"... በሚል ገዢ ሃሳብ ባልደረባችን መኮንን ሞገሴ እና ጥላሁን አበበ (ወለላው) አብረዋችሁ ያመሻሉ። በዕለቱ መሰናዶ ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ደግሞ "የሳምንቱ ጨዋታ" በሚል እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ማህበራዊ እና የማህበራዊ ሚዲያ ትዝብቶቹን ከሸጋ ምክረ-ሃሳብ ጋር በማዋሃድ በዩቲዩብ እና በቴሌቪዥን በማቅረብ የሚታወቀው ሰመረ ባርያው ካሣዬ በቀጥታ የስልክ መስመር ውይይት ይቀላቀለናል ...
"...ሒዱ፤ መጣን!" ፲፭: "በመንደሩ ለተከሰተ ሀዘን ቴፖቻችንን ያለብሱ የነበሩ ዳንቴሎቻችን የት ናቸው?”
09 October 2023

"...ሒዱ፤ መጣን!" ፲፭: "በመንደሩ ለተከሰተ ሀዘን ቴፖቻችንን ያለብሱ የነበሩ ዳንቴሎቻችን የት ናቸው?”

ምዕራፍ ፫ - "እኛ..." ተከታታይ መሰናዶ ፩- "...ሒዱ፤ መጣን!" ንዑስ ክፍል ፫: "ማንነት ከነቃ ..."ክፍል ፲፭: "በመንደሩ ለተከሰተ ሀዘን ቴፖቻችንን ያለብሱ የነበሩ ዳንቴሎቻችን የት ናቸው?” ባልደረባችን ጥላሁን አበበ (ወለላው) ያዘጋጀላችኹ የምዕራፍ ፫ ቀዳሚ ተከታታይ መሰናዶ "...ሒዱ፤ መጣን!" ሶስተኛ ንዑስ ተከታታይ መሰናዶ "ማንነት ከነቃ..." አራተኛ ክፍል ("...ሒዱ፤ መጣን!" - ክፍል ፲፭) "በመንደሩ ለተከሰተ ሀዘን ቴፖቻችንን ያለብሱ የነበሩ ዳንቴሎቻችን የት ናቸው?” በሚል ገዢ ሃሳብ ከባልደረባችን መኮንን ሞገሴ ጋር አብረዋችሁ ይቆያሉ።
"ደርግ | አገር| እኛ  ፤ 40 | 50 | 60"
29 September 2023

"ደርግ | አገር| እኛ ፤ 40 | 50 | 60"

“ያነበባችሁትን ሰምተናል፤ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት … የኢትዮጵያን ታሪክ ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል፤ አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ‹አሁን ተራው የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ!”ንጉሰ ነገሥት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም፤ ከ 49 ዓመታት በፊት...
“አሮጌ እና አዲስ ፤ ወረት እና እውነት!”
29 September 2023

“አሮጌ እና አዲስ ፤ ወረት እና እውነት!”

“አሮጌ እና አዲስ ፤ ወረት እና እውነት!”የእንዶድ የጳጉሜን ልዩ መሰናዶ-2“አሮጌው የተባለውና ከቅጽበት በፊት የነበረው ዓመት - እውነት አሮጌ ነው ወይ…? ሰው መሆንን፣ ማህበረሰብ መሆንን ለምን ማመን ከበደን? ትንሽ የእውነት ቦታ… ትንሽ ያለመሸነጋገል ቦታ… አያስፈልገንም ወይ?”በጳጉሜን አንዱ "ቅፅበት - ቀን - ዓመት ፤ የቱ ነው አዲስ?" መሰናዶ የጀመርነው አብሮ መጠየቃችን ዛሬም ይቀጥላል፤ የዝግጅት ክፍሉ ጥላሁን አበበ (ወለላው)ን እና መኮንን ሞገሴን ለዛሬው የጳጉሜን 4 ልዩ መሰናዶ ወክሏል! ታዲያ ብቻቸውን አይደሉም፣ ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድሕን በነሐሴ 1989 ዓ.ም በጻፈው “እንኳን አደረሰህ አሉ?”...