“አሮጌ እና አዲስ ፤ ወረት እና እውነት!”
የእንዶድ የጳጉሜን ልዩ መሰናዶ-2
“አሮጌው የተባለውና ከቅጽበት በፊት የነበረው ዓመት - እውነት አሮጌ ነው ወይ…? ሰው መሆንን፣ ማህበረሰብ መሆንን ለምን ማመን ከበደን? ትንሽ የእውነት ቦታ… ትንሽ ያለመሸነጋገል ቦታ… አያስፈልገንም ወይ?”
በጳጉሜን አንዱ "ቅፅበት - ቀን - ዓመት ፤ የቱ ነው አዲስ?" መሰናዶ የጀመርነው አብሮ መጠየቃችን ዛሬም ይቀጥላል፤ የዝግጅት ክፍሉ ጥላሁን አበበ (ወለላው)ን እና መኮንን ሞገሴን ለዛሬው የጳጉሜን 4 ልዩ መሰናዶ ወክሏል! ታዲያ ብቻቸውን አይደሉም፣ ብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድሕን በነሐሴ 1989 ዓ.ም በጻፈው “እንኳን አደረሰህ አሉ?” በተሰኘው ጠያቂ ግጥሙ ውክልና፤ እንዲሁም ገጣሚው፣ ተርጓሚው፣ ዓርታዒው እና ደራሲው ነቢይ መኮንን “ትንሽ ቦታ” በምትለው ዘመን አይሽሬ ግጥሙ እንደራሴነት አብረን ይቆያሉ።