ማሕደረ ዜና፣አንድ ዓመት ከትራምፕ «አሜሪካ ትቅደም» መርሕ ጋር
26 January 2026

ማሕደረ ዜና፣አንድ ዓመት ከትራምፕ «አሜሪካ ትቅደም» መርሕ ጋር

DW | Amharic - News

About
ዋይት ሐዉስ ላወጣዉ ዘገባ በ365 ቀናት 365 ድሎች የሚል ርዕሥ ሰጥቶታል።ከ365ቱ ድሎች ቀዳሚዉ የአሜሪካ የምጣኔ ሐብት ዕድገት አይደለም።ትራምፕ ሥደተኞችን ለማባረር ያወጁት ደንብ ገቢራዊነት እንጂ።በዘገባዉ መሠረት ባለፈዉ አንድ ዓመት «ሕገ ወጥ» የተባሉ 2.6 ሚሊዮን ሥደተኞች አንድም ተይዘዉ ሁለትም መታሰርን ፈርተዉ ከአሜሪካ ተባርረዋል።