በሱዳን ጦርነት የጎረቤት ቻድ ሚና
28 February 2026

በሱዳን ጦርነት የጎረቤት ቻድ ሚና

DW | Amharic - News

About
በሱዳን የሚካሄደው ጦርነት ወደ ጎረቤት ቻድም እየተቃረበ ነው። ያለፈው ሳምንት መጨረሻ የሱዳን ጦር እና አጋሮቹ በድንበር ላይ ከሚገኙት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በእንግሊዝኛው ምህፃሩ የRSF ሚሊሻዎች ጋር ተጋጭቷል። የቻድ መንግስትም ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን 1,300 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ድንበር ዘግቷል።