07 May 2021
በክርስቶስ ኢየሱስ ማረፍ
በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሰንገባ ከምንቀበላቸው የመዳን በረከቶች አንዱ የነፍስ እረፍተና ሰላም ነው::በዚህ ምድር እረፍት ለማግኘት ሰዎች በብዙ ይደክማሉ:: ስጋን ከማሳረፍ ያለፈ ነፍስን የሚያሳርፍ ግን ምንም ማንም የለም:: ነገር ግን ሰላሜን እሰጣችኃለሁ እኔ የምሰጠው ሰላም አለም እንደሚሰጥ አይደለም ያለው እርሱ ጌታ ኢየሱስ ብቻ የነፍስን ይሰጣል::- ይህም የጌታ ሰላምና እረፍት ቃሉን በመስማት እርሱ የተናገረንን በእምነት በመቀበልና እንደ ፈቃዱም በመሆን አነዲሁም ሁልጊዜ በእርሱ ፊት በመሆን በቃሉና በፀሎት በመትጋት ወደ ነፍሳችን ይፈሳል::