ለጌታ ጉብኝት ዝግጅት የሉቃስ ወንጌል 10:38-42
09 September 2021

ለጌታ ጉብኝት ዝግጅት የሉቃስ ወንጌል 10:38-42

መጋቢ ዘካርያስ በላይ

እግዚአብሔር ሰውን የሚጎበኘው በራሱ ጊዜ ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ የሆነ ሰው ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ጉብኝት የነቃ ነው፣ ዘወትር በመንፈሱ ውስጥ ስንሆን ከሐጢያት እየሸሸን በምናየውና በምንሰማው ስፍራችንን ሳንለቅ ተረጋግተን በንቃት እንኖራለን፣ በጌታ ከመጎብኘት የሚያጎድለን አንዱ አለመዘጋጀት ነው፣ ብዙዎቻችን እንጸልያለን እናመልካለን ደግሞም እናገለግላለን ለጌታ መገኝት ግን የነቃን አይደለንም ይህ ከአርሱ ጉብኝት ውጪ ያለው አደራረጋችን ይለመድና እርሱ ሊጎበኘን በመካከላችን ሲመላለስ አንረዳውም፣