የገላትያ መልዕክት 6:1-18
03 January 2021

የገላትያ መልዕክት 6:1-18

Donatist

ክርስትና የግለኝነት ህይወት አይደለም:: የተጠራነው ደግሞም የምንኖረው ለአካሉ ነው:: የአንዱን መከራ ሌላው እየተሰማው በፀጋው አቅም የምንኖረው ኑሮ ነው:: በፀጋው ለመኖር መረጥን ማለት ደግሞ ለመስቀሉ በቃን ማለት ነው:: መሰቀልን ያራቀ ደግሞም ወደ ህግ ዘወር ያለ ህይወትና ኑሮ እውነተኛውን የወንጌል ኑሮ እየኖረ አይደለም::