የእግዚአብሔር ገንዘቦች መሆን::
11 May 2021

የእግዚአብሔር ገንዘቦች መሆን::

ፓስተር ጥሩወርቅ

እግዚአብሔር ለህዝቡ የማይለወጥ ፍፁም ፍቅር አለው:: እርሱ ለእኛ ያለው ይህ መውደድ የሚገለጠው ግን እኛ በጠበቅነውና በእኛ መንገድ ሳይሆን ለእኛ በሚጠቅመን እርሱንም በምናከብርበት መንገድ ይገለጣል:: እግዚአብሔር እንደሚወደን በቃሉ ተፅፎልናልና እንደ ቃሉ እንደምንወደድ ልናምን አስፈላጊና ዋና ነገር ነው:: አለበለዚያ ለጊዜው ከሚከሰቱ ሁኔታዎች ተፅዕኖ ስር አንሆናለን:: በእግዚአብሔር ለመወደዳችንም ተጠራጣሪዎች ያደርገናል:: ይህ ደግሞ ሰላማችንን የሚጎዳ ጌታንም ደስ የማያሰኝ ህይወት ይሆናል:: እግዚአብሔር አመፀኛውን እንደሚቀጣ የእርሱን ጉብኝት በተዕግስት የሚጠብቀውን ፃድቁን በመከራ ውስጥ ይጠብቀዋል:: ፅድቁን በሚገልጥበትና በሚሰራበት ጊዜ ገንዘቡ የሆናል:: ከችግሩ በላይ በእርሱ ላይ ያለውን የጌታ መውደድ አይቷልና::