እግዚአብሔር በመንገዱ ይባርካል
14 May 2021

እግዚአብሔር በመንገዱ ይባርካል

Donatist

እግዚአብሔር በመንገዱ ፃድቅ የሆነ እውነተኛ አምላክ ነው:: ስለዚህም ሰውንም በእርሱ መንገድ እንዱሄድ ይፈልጋል:: የሰው በረከት ፈውሰና ጉብኝት ያለው በእግዚአብሔር መንገድ ላይ በሆነበትና በተገኘበት መጠን ነውና:: በዋጋ ተገዝተናልና የራሳችን አይደለንም:: ስለዚህ መንገዳችን ደግሞም በረከታችን ያለው የጌታ መንፈስ በሚመራንና በሚያስኬደን በኩል ነው::ከዚህ የወጣ ለጊዜው መልካምና በረከት የሞላበት ይምሰል እንጂ ፍፃሜው ኪሳራና ውድቀት ነው:: በእግዚአብሔር መንገድ እንሁን እንጂ ነገሮች ያልተሳኩ ደግሞም ጉድለትና እጥረት ያለበት ኑሮ ቢመስልም እንኳ የጌታ ጉብኝትና በረከት በራሱ መንገድ በጊዜው ይሆናል:: በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ሰላምና እረፍት እምነትና ተስፋ የሞላው ህይወት ይሆንልናል::