
About
በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ማንነት ሲኖረን ጌታ ከማንኛውም ክፉ ነገር ይታደገናል፣ ጸሎታችንም የሚሰማው በእግዚአብሔር ስንታይ ነው፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ማንነት እንዲኖረን ቅንነትና እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ለቃሉ የምንታዘዝ መሆን አለብን፣ ያለ ቅንነት በእግዚአብሔር ፊት የሚታይ ማንነት የለንም፣ ዛሬ ከብዙዎቻችን ቅንነት ጠፍቶ እንኳን አንገነዘበውም፣ ግን ሲጎድልብን እናያለን፣ ነገሮች ሲከብዱብን ጸሎታችን አልሰማ ሲል መውደድ ሲያቅተን መራራትና ምህረት ማድረግ ሲያቅተን፣ ይህን ሁሉ በዘመናችን እያየን ስለሆነ፣ ከመቼውም በበለጠ በፊቱ ሞገስ የምናገኝበትን ጸጋ መለመን አለብን፣