
About
የአንድ አማኝ ዕድገት ትልቅ ከፍታ እኔ የጌታ ነኝ ማለት መቻሉ ነው፣ የተፈጠርነው የእግዚአብሔር ለመሆን እንደሆነ ሲገባን የመከራና የችግሮች መደራረብ ከክርስቶስ ፍቅር እየነጠሉን ሳይሆን የእርሱ መሆናችንን እያስረገጡልን ነው የሚሄዱት፣ እግዚአብሔርም ከጥንት ከመጀመሪያው የእርሱ ስላደረገን ባለቀቅነው ማንነታችን ወይም የእርሱ ሆንን ባልተገኘንበት የእርሱ ሆነን እስክንገለጥ ወደ እርሱ የሚይስጠጋንን የህይወት ማዕበልና ወጀብ ይፈቅዳል፣