ድሪብል ሬድዮ በየአብ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን የተቋቋመ የኦንላይን ራዲዮ ነው። የድሪብል ኦንላይን ሬድዮ ዋና አላማ በኢትዮጵያ በጤና፣ በስፖርት፣ በመዝናኛ፣ እና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያለውን የመረጃ ክፍተት መሙላት ነው። አሁን ድሪብል ኦንላይን ሬድዮ በመላው አለም ስርጭታችንን በቀጥታ ስርጭት በማሰራጨት በሂደት ላይ እንገኛለን። ራዕያችን ሩቅ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ የደስታ ስሜቱን እና መረጃውን እንዲያካፍልን መልካም ዜና እንሰብካለን።