
About
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያቀረቡትን ክስ ዛሬ ሰኞ “ሐሰት” በማለት አጣጥሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በደብዳቤያቸው የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ሰሜን ምሥራቅ የድንበር አካባቢ ከዚህ ቀደም ከተቆጣጠሩት “የበለጠ ዘልቀው” እንደገቡ ገልጸው ነበር። በጉዳዩ ላይ የተንታኞች እና የፓለቲከኞች አስተያየቶች የተካተቱባቸው ዘገባዎች ለዛሬ ተዘጋጅተዋል። የአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 625,000 የሥራ ዕድሎች በክልሉ እንደተፈጠሩ አስታውቋል። ይህን የተመለከተው ዘገባ በዜና መጽሔት ከሚቀርቡት መካከል ነው።