
About
በተለያየ ጎራ የተሰለፉ ኢትዮጵያውን በሙሉ ልብ እንደሚስማሙበት የሚናገሩለት ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ መሠረቱ በተጣለ በ14ኛ ዓመቱ በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል። በገንዘባችሁ፤ በሙያና ላባችሁ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ! ዛሬ የግድቡን ምርቃት ምክንያት በማድረግ የዜና መጽሔት ትኩረቱን በዚህ ላይ አድርጓል፤ የሕዝብ አስተያየትንም አካተናል፤ የታላቁ ኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስከያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮንም አነጋግረናል።