
About
የዜና መጽሔት ጥንቅራችን፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነዉ ሲሉ፣ -የዚያዉ ከትግራይ ክልል ወጣቶች ደግሞ አፈሳና የጦርነት ዝግጅት እንዳሳሰባቸዉ እያስታወቁ ነዉ።የዳግም ጦርነት ዝግጅት፣ ወቀሳና ሥጋቱን ዜና መጽሔቱ በሁለት ዘገቦች ያስተነትናል።የኢትዮጵያ ምርጫ የጥቃት ኢላማ እንደነበር፣ የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ግን ዘንድሮም በ10.2 በመቶ አድጓል መባሉ ከወደ አዲስ አበባ ተሰምቷል።ሌላዉ የዜና መፅሔት ርዕስችን በሱዳንዋ ሥልታዊ ከተማ አል-ዑቤይድ የተፈፀመዉ የመብት ጥሰትና ይደርሳል የተባለዉ ተጨማሪ ጥፋት የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ኮሚሽንን እያባተለ መሆኑን ይቃኛል።