
About
ዛሬ ታስቦ የዋለዉን 85ኛ የኢትዮጵያዉያን የድል በዓል መታስብያን በማስታከክ ፤ የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም ሲል የሚያጠይቅ ዘገባን ይዘናል። ለ7ኛዉ ጠቅላላ ምርጫ ቅስቀሳ ተግዳሮት ገጠመን ያሉ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በደቡብ ወሎ ዞን እንዲሁም በኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የመሸጫ ዋጋ ጭማሪ እና የሚያሳድረዉ ጫናን የሚዳስስ ዘገቦችም በተከታታይ ይቀርባሉ። የአሜሪካዉ ትራምፕ በጀርመን ከሰፈሩ የአሜሪካን ወታደሮች መካከል ወደ 5,000 የሚሆኑትን ለማስወጣት እቅድ መያዛቸዉ እና የተሰጡ ግብረ መልሶችን የሚዳስስ ዘገባንም ይዘናል።