About
የዜና መጽሔት: ኢትዮጵያና ግብፅ በዓባይ ወንዝ ዉኃ አዘቃቀም ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ ሞቅ ቀዝቀዝ እንዳለ መቀጠሉን የሚቃኘዉን ዘገባ ያስቀድማል። ከወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ሥጋት ባንዣበበት ባሁኑ ወቅት የደቡብ ወሎ ወጣቶች፣ የአቅመ-ደካሞችን ቤቶች መጠገንን ጨምሮ ለየአካባቢያቸዉ ሕዝብ 1.4 ቢሊዮን ብር የሚገመት ነፃ አገልግሎት መስጠታቸዉ ተዘግቧል።ለጋምቤላ በተለይ ለኑዌር ዞን የዘንድሮዉ ክረምት የድርቅ ሥጋት አስከትሏል።ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የወባ በሽታ አለቅጥ ተዛምቷል።ጀርመን ለአፍሪቃ ሕብረት የሰጠችዉ የገንዘብ ድጋፍ የአፍሪቃ ሐገራትን ድንበሮች ለማካለል እየጠቀመ መሆኑ ከአዲስ አበባ ተሰምቷል።