የመስከረም 1 ቀን 2018 የዓለም ዜና
11 September 2025

የመስከረም 1 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
-ኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጪያ በዓልን ዛሬ አክብረዉ ዉለዋል።አዲሱ ዓመት ታላቁ የሕዳሴ ግድብ በተመረቀ ሳልስት በመዋሉ የድርብ በዓል ስሜት ተላብሷል።ይሁንና እስከ አምና ማብቂያ የቀጠሉት ግጭቶች፣ጥቃቶች፣ እገታና ዘረፋዎች ይቀጥላሉ የሚለዉ ሥጋት፣በዓሉን ስሜት በሥጋት አቃርጦታል።--የአፍሪቃ የአየር ንብረት ጉዳይ ጉባኤ አፍሪቃ የዓየር ንብረት ቀዉስን ለማስወገድ ለነደፈችዉ ዕቅድ በየዓመቱ 50 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልጋት አስታወቀ።-የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች መዘጋት፣ የኑሮ ዉድነት፣ ሥራ አጥነትና ሙስና ያስመረራቸዉ የኔፓል ወጣቶች የጀመሩትን አመፅ እንደቀጠሉ ነዉ።