
About
ቤኒሻንጉል፥ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር ውስጥ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ማሰልጠኛ መገንባቱ ተዘገበ፤ ጄኔቫ፥ ተመድ በትግራይ ክልል ውጥረቱ እንዲረግብ ጥሪ አስተላለፈ፤ አ.አ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በግማሽ ዓመት 4.4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ፤ ባሕር ዳር፥ በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ 19 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለ7ኛው አገራዊ ምርጫ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፤ ጄኔቫ፥ ተመድ ሱዳን ውስጥ ሕጻናት ለከፍተኛ ረሐብ ተጋልጠዋል ሲል አስጠነቀቀ፤ በሊቢያ የባሕር ጠረፍ በደረሰ የጀልባ አደጋ 53 ስደተኞች መሞታቸው አለያም መጥፋታቸው ተዘገበ