Opens in a new window
የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓም ረቡዕ
08 July 2026

የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 01 ቀን 2018 ዓም ረቡዕ

የዓለም ዜና

About
አርስተ ዜና፤ የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስና ወታደራዊ ኃይል በጆሃንስበርግ አቅራቢያ በሕገ-ወጥ የማዕድን ቁፋሮ ሥራዎች ላይ ባደረጉት ከፍተኛ ዘመቻ ከ200 በላይ ሰዎችን አሰሩ። በደቡብ አፍሪቃ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መካከል ህጋዊ ወረቅት የሌላቸዉ ስለመያዝ አለመያዛቸዉ እስካሁን የወጣ ግልፅ መረጃ የለም።-የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኔቶ ስብሰባ አንካራ ተገኝተዋል። ትራምፕ ድርጅቱ ባሳየዉን ወታደራዊ ኤግዚቢሽን የተደሰቱ አይመስልም። የአውሮጳ ህብረት ሀገራት ኔቶን ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረትና የኢራን ጦርነት ለመቀላቀል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ትራምፕ በተደጋጋሚ ተችተዋል።