Opens in a new window
DW Amharic የሐምሌ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና
11 July 2026

DW Amharic የሐምሌ 04 ቀን 2018 የዓለም ዜና

የዓለም ዜና

About
አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለስድስት አገራት ዜጎች የተሰጠውን በአገሪቱ የመቆየትና የመሥራት ጊዜያዊ ከለላ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመች። የሱዳን ብሔራዊ ጦር አሜሪካ ያዘጋጀችውን ምክረ-ሐሳብ የሚቀበለው ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከተቆጣጠራቸው ከተሞች ለቅቆ ሲወጣ እንደሆነ ቅድመ-ሁኔታ አስቀመጠ። የናይጄሪያ ጦር በዛምፋራ ከ300 በላይ ታጣቂዎች ገደለ ተባለ። የኢራን መንፈሳዊ መሪ ሞሽታባ ኻሜኒ አገራቸው የአባታቸውን ገዳዮች መበቀሏ “አይቀሬ” እንደሆነ ዛቱ። የአሜሪካው ፕሬዝደንት በኢራን ላይ ያነጣጠሩ 1,000 ሚሳይሎች መጠመዳቸውን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመቻቸው ጥቃቶች ስድስት ሰዎች ሲገደሉ 29 ቆሰሉ።